Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የዓለም ዋንጫ ውድድር በታሪክ ምርጡ ይሆናል ብለዋል

SM Samuel Mulgeta Jun 11, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 208 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የዓለም ዋንጫ ውድድር በታሪክ ምርጡ ይሆናል ብለዋል

በታሪክ መነጋገሪያ የሆነው የ2026 ዓለም ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል።

በመኮነን አልማው!

 

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት አዘጋጅነት የሚካሔደው 23ኛው የአለም ዋንጫ ውድድር ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በሜክሲኮ መካሄዱን ሲጀምር አዘጋጇ ሀገር ሜክሲኮ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ትጫወታለች።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


ሜክሲኮ በአለም ዋንጫ ታሪክ በመክፈቻ ያደረገቻቸውን ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለችም። ሜክሲኮ ያኔ 2010 የደቡብ አፍሪካው ዓለም ዋንጫ ጊዜ ከራሷ ከአዘጋጇ ጋር የመክፈቻ ጨዋታዋን አድርጋ 11 ነበር የተለያዩት።


ዛሬ በሀገሯ 2010 የአለም ዋንጫ አዘጋጇ አፍሪካዊት ሀገር ጋር የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። በዚህ አለም ዋንጫ በሶስቱም አዘጋጅ ሀገራት በኩል ሶስት የመክፈቻ ጨዋታ የሚካሔድ ሲሆን የመጀመሪያው መክፈቻ ዛሬ ምሽት ይደረጋል።


በመክፈቻው ሻኪራ እና ቡርና ቦይ ' dai dai ' የተሰኘውን ይፋዊ የዓለም ዋንጫ ዜማ ያቀነቅናሉ። እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ አቀንቃኞች ይገኛሉ።



በዘንድሮው የመክፈቻ ዝግጅት ዶናልድ ትራምፕ እንደማይገኙ ተገልጿል።


በዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ የአዘጋጅ ሀገራት መሪዎች ስታዲየም ሲገኙ መመልከት የተለመደ ቢሆንም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የአሜሪካ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ የመገኘት እቅድ እንደሌላቸው ተገልጿል።



በመክፈቻ ጨዋታው እሳቸውን በመተካት ሌሎች ሀላፊዎች እንደሚገኙ ተነግሯል። ባለፉት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች መክፈቻ ጨዋታ ላይ የአዘጋጅ ሀገራት መሪዎች ተገኝተው ነበር።



ለአብነትም :- 2022 አለም ዋንጫ የኳታር ጠቅላይ ምኒስትር ኤሚር ተገኝተው ነበር። 2018 አለም ዋንጫም የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በመክፈቻው መገኘታቸው ይታወሳል። እንዲሁ 2014 የአለም ዋንጫ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሮሴፍ ተገኝተው የሀገራቸውን መክፈቻ ጨዋታ ታድመው ነበር።



አሜሪካ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታዋን ነገ አርብ ሌሊት 10:00 ሰዓት ከፓራጓይ ጋር ታደርጋለች። ገና ከወዲሁ አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ የሆነው ይህ የአለም ዋንጫ ውድድር በበርካቶች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ እየተተቸ ሲሆን ትራምፕ እና ኢንፋንቲኖም ምላሽ ሰጠውበታል።



የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የዓለም ዋንጫ ውድድር በታሪክ ምርጡ ይሆናል ብለዋል።



"
ኢንፋንቲኖም በታሪክ እንዲህ ሰምሮ አያውቅም ብሎኛል" የሚሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ዓለም ዋንጫ ያላቸውን አስተያየት ስጥተዋል።



በንግግራቸውም2026 ዓለም ዋንጫ በታሪክ ስኬታማው ዓለም ዋንጫ ይሆናልያሉት ፕሬዚዳንቱ ስለ ቪዛ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ከጋዜጠኞች ተጠይቀው ሲመልሲ  “ጥሩ ሰዎች ብቻ ወደ ሀገራችን እንዲገቡ ተግተን እየሰራን ነውሲሉ መልሰዋል።



የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው ትላንት ምሽት በሜክሲኮ ስለውድድሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።



ጂያኒ ኢንፋንቲኖ 3 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር በተገናኙበት በዚህ ቆይታ "ዓለም ዋንጫው ሁሉንም ሪከርድ ይሰብራል" ሲሉ ተናግረዋል።

 


"
የዘንድሮውን የአለም ዋንጫ ውድድር ከሁሉም የተለየ ነው" የሚሉት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ስለ ትኬት ዋጋ ተጠይቀው ሲመልሱየዚህ አመት የአለም ዋንጫ ትኬት ፍላጎት አይተነው የማናቀው ነው። ካለፉት ውድድሮች በአስር አጥፍ ይበልጣልብለዋል።



የዓለም ዋንጫ አዘጋጅነቱን ለአሜሪካ በመስጠታቸው ይፀፀቱ እንደሆነ ተጠይቀው የተጠየቁት ኢንፋንቲኖበፍፁም አልፀፀትምሲሉ ምላሽ የሰጡ ሲሆን  “ የምፀፀትበት አንዳችም ነገር የለምብለዋል።



ስለ ቪዛ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱአሜሪካ ማንን ወደ ሀገሯ ማስወጣት እና ማስገባት እንዳለባት እኛ መወሰን አንችልምሲሉ መልሰዋል። በአዘጋጆች ይህ የተባለለት ነገር ግን በተመልካቹ እና በተሳታፊዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተተቸ ያለው ይህ የአለም ዋንጫ ዛሬ በይፋ መካሔድ ይጀምራል።



በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የሚደረገው የዕለቱ 2026 ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታው በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም ከምሽቱ 4:0 ሰዓት ላይ ይጀመራል።



የመክፈቻ ጨዋታውን ብራዚላዊው ዳኛ ዊልተን ሳምፓዮ በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።



ከዚህ የመክፈቻ ጨዋታ ቀጥሎ ሌሊት 11 ሰዓት ላይ ደቡብ ኮሪያ ከቼክ ሪፐፕሊክ ይጫወታሉ።




 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

56 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።