Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

ቱጃሩን ክለብ ከመድፈኞቹ የሚያገናኘው የፍፃሜ ፍጥጫ

SM Samuel Mulgeta May 30, 2026 3 ደቂቃ ንባብ 118 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ቱጃሩን ክለብ ከመድፈኞቹ የሚያገናኘው የፍፃሜ ፍጥጫ

እኛም ይህን ጨዋታ ከገበያ ሚዲያ ስቱዲዩ በቀጥታ በኢትዮ ግሎባል የዩቲዩብ ገጽና፣ በገበያ ሚዲያ የፌስቡክ እና የቲክቶክ ፔጅ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል። ለተሳታፊዎች ያዘጋጀነው ሽልማትም አለ፡፡


ፒኤስጂ ወይስ አርሰናል ማን ይነግሳል?

 

 በመኮንን አልማው

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

2025/26 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ ተወካይ ክለቦች መካከል ይደረጋል፡፡



የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኖቹን ይፋለማል፡፡


የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በበኩሉ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ወደ ኤሜሬትስ ለመውሰድ ከፈረንሳዩ ክለብ ከባድ ፍልሚያ ይጠብቀዋል።



አስፈሪ የፊት መስመር ጥምረት ያለው ፒኤስጂ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ድረስ 44 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡ በተቃራኒው 22 ግቦች ደግሞ ራሡ ላይ የተቆጠሩበት ሲሆን 5 ጨዋታዎች ግብ ሳያስተናግድ ወጥቷል።



አርሰናል በበኩሉ 29 ግቦችን ተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥር 6 ግቦች ብቻ ተቆጥረውበታል፡፡ በዚህም በውድድሩ መድረክ በጣም ትንሽ ግቦች የተቆጠረበት ክለብ ያደርገዋል።



በተጨማሪም መድፈኞቹ 9 ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው የወጡ ሲሆን በውድድሩ አንድም ጨዋታ አልተሸነፉም።



በዚህም መድፈኞቹ በውድድር ዓመቱ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ ጠንካራ የመከላከል ክፍል ካላቸው ቡድኖች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።


በወቅቱ የባላንዶር አሸናፊው ኦስማን ደንቤሌ፣ ክቫራትስኬሊያ  እና በዲዜሬ ድዌ አስፈሪው የፒኤስጂ የፊት መስመር ጥምረት በምሽቱ የፍፃሜ ፍልሚያ ለጠንካራው የአርሰናል የተከላካይ ክፍል ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡



ጉዳት ላይ የነበሩት የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች ኦስማን ዴምቤሌ እና አሽራፍ ሀኪሚ ወደ ልምምድ የተመለሱ ሲሆን አርሰናልን የሚገጥመው የፒኤስጂ ስብስብ ውስጥ ተካትተዋል፡፡


በመድፈኞቹ በኩልም በጉዳት ላይ የቆየው ጁሪየን ቲምበር በበኩሉ በምሽቱ ጨዋታ ለመድፈኞቹ ግልጋሎት ይሰጣል።

 

ይህንን አለም በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቀው ያለውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ 43 ካሜራዎች ከተለያዩ አንግሎች ሆነው እንደሚቀርፁ ተረጋግጧል። ይህም በውድድሩ ታሪክ የታየ ከፍተኛ ቁጥር ሲሆን በመደበኛ የሊግ ጨዋታዎች ከሚደረገው 20 ካሜራዎች በእጥፉ በልጧል።



በዚህ ጨዋታ የሁለቱም ክለቦች በርካታ ደጋፊዎች በቦታው ተገኝተው ለክለባቸው ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።



በዚህ በኩል የፈረንሳዩ ቱጃር ክለብ ፒኤስጂ በርካታ ደጋፊዎችን በነፃ ወደ ቡዳፔስት እንዲጓዙ አድርጓል።



በዚህም 20,000 የፒኤስጂ ደጋፊዎች የሚጠበቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 17,000 ያህል የሚሆኑት ቀድመው ትኬት ማግኘታቸውን በሀንጋሪ የፈረንሳይ ኤምባሲ ከአንድ ቀን በፊት አሳውቋል።


የፒኤስጂው ፕሬዝዳንት ናስር አል ካሊፊ በበኩላቸው ለፍፃሜ ጨዋታው ቀደም ብለው ወደ ሀንጋሪ አቅንተዋል።



እንዲሁም ለክለቡ ተጨዋቾች ሞቅ ያለ የገንዘብ ጉርሻ አዘጋጅተዋል።



የፒኤስጂ ፕሬዝዳንት የሆኑት ናስር አልካላፊ ፒኤስጂ አርሰናልን አሸንፎ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫውን የሚያነሳ ከሆነ ለእያንዳንዱ ተጫዋች €1 ሚሊየን ዩሮ ማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።


በዚህ ጉርሻ ዙሪያ ማርኩኒሆስ ዴምቤሌ ሀኪሚ እና ቪቲኒሀ ከክለቡ አስተዳደር ጋር መደራደራቸው ተነግሯል። ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር አመት በተመሳሳይ ለተጨዋቾቹ ጉርሻ አዘጋጅቶ የነበር ሲሆን ሻምፒዮንም ሆኗል።



በአርሰናል በኩል ግን ምንም አይነት የደጋፊ ስፖንሰር ስለመደረጉ የተሰማ ነገር የለም።



አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባነሳበት ዓመት የቻምፒየንስ ለግ ዋንጫን ማሸነፍ ከቻለ 4ኛው የእንግሊዝ ክለብ ይሆናል።



ሁለቱን ዋንጫዎች በአንድ አመት አንድ ላይ ማሳካት የቻሉት በታሪክ ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ናቸው።



የእንግሊዝ ክለብ በአንድ አመት ፕሪሚየር ሊጉን እና ሻምፒየንስ ሊጉን ያሸነፈበት ውጤት የተመዘገበውም አምስት ጊዜ ነው።



ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን ማድረግ የቻለው 2022/23 የውድድር ዘመን ማንችስተር ሲቲ ነበር።



ከዚህ በፊት ሊቨርፑል 1983/84 ማንቸስተር ዩናይትድ 1999 እና 2008 እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ 2023 ይህንን ማድረግ ችለው ነበር።



ፒኤስጂ በበኩሉ ዛሬ ምሽት የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያሸንፍ ከሆነ የሪያል ማድሪድን ታሪክ ይጋራል።



በሻምፒየንስ ሊጉ ታሪክ ለሁለት ተከታታይ አመታት ዋንጫውን ማሸነፍ የቻለው ብቸኛ ክለብ ሪያል ማድሪድ ነው።



ሎስ ብላንኮዎቹ 2016 - 2018 በተከታታይ ሶስት ጊዜ ማሸነፍ ችለው ነበር።



በዛን ዘመንም ቢሆን ሪያል ማድሪድ 1956 - 60 በተከታታይ አምስት ጊዜ በማሸነፍ መቆጣጠር ችለው ነበር።



ይህ አለም በጉጉት የሚጠብቀው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ የእንግሊዙ አርሰናል ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በሀንጋሪ ቡዳፔስት   በፑስካሽ አሬና ስቴዲየም ይደረጋል።



እኛም ይህን ጨዋታ ከገበያ ሚዲያ ስቱዲዩ በቀጥታ በኢትዮ ግሎባል የዩቲዩብ ገጽና፣ በገበያ ሚዲያ የፌስቡክ እና  የቲክቶክ  ፔጅ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

 

በቆይታችንም ጨዋታውን በቀጥታ ኮመንተሪ እና በሰፊ ትንታኔ ከመከታተል ባሻገር በሽልማት የሚያንበሸብሹ የጥያቄ እና መልስ ጊዜ ይኖረናል።




 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

32 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።