Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

በአዲሱ በጀት ውስጥ የደመወዝ ጭማሪ እቅድ ታሳቢ እንዳልተደረገ አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ!

SM Samuel Mulgeta Jun 11, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 280 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በአዲሱ በጀት ውስጥ የደመወዝ ጭማሪ እቅድ ታሳቢ እንዳልተደረገ አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ!

የመንግስት ሠራተኞች በኑሮ ውድነት ምክንያት እያቀረቡት ያለውን የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት እቅድ ላይ ጥያቄ አንሰተዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በተለይም በበጀት ሰነዱ ውስጥ "ልዩ ልዩ ወጪዎች" በሚል የተመደበው ከፍተኛ ገንዘብ ግልጽነት እና ለደመወዝ ጭማሪ የተያዘው እቅድ ላይ ማብራሪያ ጠይቀዋል።



ባለፈው አመት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄዎች ቀርበው "የለም" የሚል ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ጭማሪ ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት / ደሳለኝ ዘንድሮም ተመሳሳይ ሁኔታ ስለመኖሩ አስቀድመው ጠይቀዋል።



በዚህም በኢኮኖሚው ላይ እየተፈጠረ ባለው የኑሮ ውድነት ጫና የመንግስት ሠራተኞች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዱ መሆናቸውን በመጥቀስ መንግስት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን አስመልክቶ በበጀት እቅዱ ላይ ያካተተው ነገር መኖሩን ነው የጠየቁት።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


በተጨማሪም በመደበኛው በጀት ውስጥ የተመደበው 904 ቢሊዮን ብር "ልዩ ልዩ ወጪዎች" በሚል መመዝገቡ አጠያያቂ እንደሆነ / ደሳለኝ ተናግረው ከዚህ ውስጥ ለአስተዳደር፣ ለኢኮኖሚ እና ለማህበራዊ አገልግሎቶች የሚውለው ድርሻ እንዲሁም ለትምህርትና ለጤና የተመደበው 126 ቢሊዮን ብር በቂ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።



የበጀት ሰነዱ ዘግይቶ እንደደረሳቸው የገለጹት / ደሳለኝ ይህ ከፍተኛ የበጀት ድልድል ለዕዳ ክፍያ ነው ወይስ ለሌላ ዓላማ የሚል ጥያቄያቸውን አቅርበው መንግስት በልዩ ልዩ ወጪዎች ስም የተመደበውን በጀት ዝርዝር እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል።



ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው መንግስት ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ለዝቅተኛ እና ቋሚ ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ መሻሻል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።



በተለይም የደመወዝ ጭማሪው በገንዘብ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጥንቃቄ መከናወኑን ጠቅሰው የደመወዝ ጭማሪው በተደረገበት ወቅት ክልሎች ከተመደበላቸው በጀት ጋር ተያይዞ ተግዳሮቶች ተፈጥረው እንደነበር ገልጸዋል።



በተጨማሪም "የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ እና ለክልሎች የተሰጠው የበጀት መጠን አይመጣጠንም በሚል ጥያቄዎች ሲነሱ ነበር፤ እኛም ይህንን ችግር ስናጠራ ቆይተን አሁን በመፍታት ላይ እንገኛለን" ብለዋል።


አቶ አህመድ ሽዴ አክለውም አሁን ለምክር ቤቱ የቀረበው በጀት የፌዴራል መንግስትን ብቻ ሳይሆን የክልል መንግስታትንም የደመወዝ ጭማሪ አካቶ የያዘ መሆኑን ገልጸው ከዚህም በተጨማሪ እስከ 5 በመቶ የሚጠጋ ተጨማሪ ጭማሪ በማካተት የፌዴራል መንግስትን የወጪ ጫና መሸከሙን አስረድተዋል።



በቀጣይ ዓመት ስለሚኖር የደመወዝ ጭማሪ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ በዘንድሮው በጀት ውስጥ ተጨማሪ የደመወዝ ጭማሪ እቅድ ታሳቢ እንዳልተደረገ ገልጸው "በቀጣይ ምን ይታሰባል የሚለው ጉዳይ አሁን በቀረበው በጀት ታሳቢ አልተደረገም፤ ይህ መታወቅ ይኖርበታል" በማለት ተናግረዋል።


መንግስት የሠራተኞቹን ደመወዝ በማስተካከል ረገድ የነበረበትን ከፍተኛ የገንዘብ ጫና በመወጣት ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተወጣ የገለጹት አቶ አህመድ ሽዴ በበጀት እቅዱ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

56 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።