Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አስተያየት

የሰሞኑ የውጪ ሚዲያዎች ዘመቻና እውነታው!

SM Samuel Mulgeta Jun 2, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 952 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የሰሞኑ የውጪ ሚዲያዎች ዘመቻና እውነታው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በትናንቱ ዕለት በተካሄደው ምርጫ በትውልድ ስፍራቸው በሻሻ ከተማ ተገኝተው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በሳሙኤል ሙሉጌታ!

 

ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫዋን ለማካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረችበት ወቅት፣ ባልተለመደ መልኩ የውጪ ሚዲያዎች ኢትዮጵያን ትኩረት ያደረጉ ዘገባዎችን ሲዘግቡ ሰንብተዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

ዘኢኮኖሚስት፣ ሲኤንኤን እና አፍሪካ ኒውስን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ላይ ያነጣጠሩ የትችት ዘገባዎችን በስፋት ሲያወጡ ቆይተዋል።

 

እነዚህ ዘገባዎች፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ካስመዘገቧቸው የዲፕሎማሲ ስኬቶች ማግስት፣ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱትን ግጭቶችና የፖለቲካ ልዩነቶች በጥብቅ የፈተሹ ናቸው።

 

ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት በምርጫው ዋዜማ ያወጧቸው ትንተናዎች በዋናነት በሀገሪቱ መረጋጋትና በዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። ዘኢኮኖሚስት መጽሔትየዐቢይ አሕመድ ኢምፓየር ራዕይበሚል ባወጣው ዕትም፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ምኞቶችና ክልላዊ አካሄዶች በሀገሪቱና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽዕኖዎች የሚተች ጽሑፍ አስነብቧል።

 

ሲኤንኤን በበኩሉ ባወጣው ሰፊ ዘገባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥልጣን መጀመሪያ ዘመናቸው የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸውንና የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸውን አስታውሶ፣ ከዚያ በኋላ ግን ሀገሪቱ ወደ ውስብስብ የብሔር ግጭቶች ማምራቷንና የፖለቲካ ምኅዳሩ መጥበቡን ጠቅሷል።

 

ይህንን የሲኤንኤን የትችት ዘገባ የግብፁ የዜና ተቋም ኢጂፕት ኢንዲፔንደንትም በቀጥታ በመውሰድ በገጹ ላይ አጋርቶታል።

 

አፍሪካ ኒውስ በበኩሉ፣ ምርጫውን ተከትሎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በነጻነት የመቀስቀስ ዕድላቸው መገደቡንና በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚነሱ ትችቶች መኖራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል።

 

ይሁን እንጂ ከእነዚህ ዘገባዎች ጀርባ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆነችው ግብጽ እጅ እንዳለበት በስፋት ይጠረጠራል። በዚህ ረገድ አንድ ዘገባን ማስታወስ ያስፈልጋል።

 

ዓለም አቀፉ የዜና ወኪል ሮይተርስኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) ወታደራዊ ዕርዳታ ትሰጣለችበማለት ያወጣውንና የኢትዮጵያ መንግሥት ፍጹም ሐሰተኛ ነው በማለት በይፋ ያስተባበለውን ዘገባ እናስታውስ።

 

ይህ ዘገባ በወቅቱ በስፋት ሲቀባበል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በኋላ ላይ ግን ይህን ዘገባ የጻፉት መቀመጫቸውን ካይሮ ያደረጉት አሌክሳንደር ዲያዶዝ፣ ናፊሳ ኤልታሂር እና አህመድ ሻላቢ የተባሉ ጋዜጠኞች መሆናቸው ታውቋል።

 

በመሆኑም ግብጽ በሎቢስት የታወቀች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ከእነዚህ ሰሞነኛ ዘገባዎች ጀርባም ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ እንደነበርና በሀገሪቱ ሁከት ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ እንደነበር መገመት ይቻላል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በትናንቱ ዕለት በተካሄደው ምርጫ በትውልድ ስፍራቸው በሻሻ ከተማ ተገኝተው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህምየኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችበምርጫው ታማኝነትና ታሪካዊ ሂደት ላይ የሕዝብ እምነት ለማጥፋት የተቀናጀ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሲያካሂዱ እንደነበር በግልጽ ከሰዋል።

 

ሆኖም ግን፣ ማናቸውም ዓይነት የሚዲያ ጫናዎችና ውጫዊ መሰናክሎች ሀገሪቱ የጀመረችውን የዴሞክራሲ ግንባታ፣ አገራዊ እርቅና የልማት ጉዞ ሊያስተጓጉሉ እንደማይችሉና እንቅፋት ሊሆኑ እንደማይገባቸው አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።

 

ዓለም አቀፍ ተቋማት የአገሪቱን የጸጥታ ስጋቶች በተደጋጋሚ ቢያነሱም፣ በትናንትናው ዕለት ከአንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር ምርጫው በተካሄደባቸው ቦታዎች መራጮች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጻቸውን ሲሰጡ ውለዋል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች የምርጫው ይፋዊ ውጤት በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

41 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።