Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

በሶማሊያዊው ዳኛ ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ድርጊት!

SM Samuel Mulgeta Jun 10, 2026 Updated 3h ago 3 ደቂቃ ንባብ 71 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በሶማሊያዊው ዳኛ ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ድርጊት!

ነገ ምሽት መክፈቻውን የሚያገኘው የ2026 ዓለም ዋንጫ በተፈጥሮ እና አሜሪካ ሰራሽ ችግሮች ጣጣው በዝቷል።

በመኮነን አልማው!

  

ተፈጥሮ በወለደው የአየር ንብረት ከፍተኛ ሙቀት እና በርዕደ መሬት ክስተት ከፍተኛ ስጋት ያለበት የ2026ቱ ዓለም ዋንጫ በልምምድ ቦታዎች የጥራት እና የደህንነት ችግርም ትችቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛል፡፡

Advertisement
Your ad could be here — contact us



ለዚህም በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ማረፊያ አቅራቢያ የተፈጠረውና 9 ሰዎች የተጎዱበት የተኩስ ሩምታ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አቅራቢያ ያለው የአደገኛ እባቦች መናኻሪያ እና የሜክሲኮ ሰዎች መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ማሰማታቸው ተጠቃሽ ነው።


እኒህን ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ክስተቶችን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮች 2026 ዓለም ዋንጫውን እያስተቹት ነው።



ሌላው የአሜሪካ የቪዛ መዘዝ ነው።



በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የምትመራዋ አሜሪካ "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ በብዙ ችግሮች የተተበተበው የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ላይ "ቪዛ" የሚል ቀይ ካርድ በመምዘዝ ሌላ ማነቆ ሆናለች። አሜሪካ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊዎች መስጠት የነበረባትን ቪዛ አለመስጠቷ የሳምንቱ መነጋገሪያ ዜና መሆኑ ግልጽ ነው።

 


ለምሳሌ:- የኢራን ተጨዋቾች   የአፍሪካ እና ኢራን ጋዜጠኞች ቪዛ መከልከል በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። እንዲሁም የሶማሊያዊው ዳኛ አሜሪካ እንዳይገባ መከልከሉ ግርምትን የፈጠረ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።


በታሪክ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ በመሆን ለዓለም ዋንጫ ውድድር ዳኝነት የተመረጠው ዑመር አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሏል።


ሶማሊያዊው ዳኛ ዑመር ትክክለኛ የቪዛ ሰነድ ይዞ አሜሪካ ቢደርስም የአሜሪካ የድንበርና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ግን ተጨማሪ ፍተሻ ካደረጉበት በኋላ "መግባት አትችልም" በማለት ወደ መጣበት እንዲመለስ አድርገውታል።



አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሎ የተመለሰው ሶማልያዊው ዳኛ ኦማር አብዱልቃድርም ዛሬ ጥዋት ሀገሩ አየር ማረፊያ ሲደርስ ህዝቡ እጅግ ደማቅ የክብር አቀባበል አድርጎለታል።



ዋና ዳኛው ከደረሰበት ክልከላ በኋላ ከመላው አለም ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘት ችሏል።



ዳኛው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክትአሁንም በጥሩ መንፈስ ላይ እገኛለሁ በቀጣይ ጉዞዬ ላይ ትኩረት አድርጌ እገኛለሁ" ብሏል። የስፖርት ቤተሰቡ ለሰጠው ድጋፍ እና የአብሮነት መግለጫ መልዕክትም ዳኛው አመስግኗል። ታዲያ ይህ የቪዛ ጉዳይ የበርካታ ሀገራትን ልዑካን ቡድን እጅግ ያማረረ እና ከህልማቸው ያጨናገፈ ሆኗል።



ለምን?



የዚህ ከፍተኛ ውዝግብ መነሻ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ዳግም ሲመለሱ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለጸ ጉዳይ ነበር።



ፕሬዝዳንቱ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካን ህዝብ ከስደተኞች ለመጠበቅ ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን በትረ-ስልጣኑን ሲቆጣጠሩም የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈው ነበር። በተለይ በበርካታ የአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ የጉዞ ክልከላን ጨምሮ በርካታ ገደቦች ተጥለው ነበር።



እነዚህ ክልከላዎች አሁን ለተፈጠረው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል። በተለይ ዛሬ ላይ ለተፈጠረው የሶማሊያዊው ዳኛ አሜሪካ እንዳይገባ መታገድ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዚህ በፊት የሰጡት አስተያየት ዋና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው።


ፕሬዝዳንቱ በአንድ ወቅትሶማሊያዎች እርስ በርስ ይገዳደላሉ! ሀገራቸው ዋጋ የላትም በሙስና ተዘፍቀዋል! እኛ እዚህ አንፈልጋቸውምብለው ነበር። ይሁን እንጂ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ባለፉት አመታት ይህ ይፈጠር እንደሆነ ሲጠየቁ ' አትስጉ ' የሚል ማስተማመኛ ሰጥተው ነበር።


ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ይህንን በሚመለከት በተለያዩ መድረኮች በጋዜጠኞች ሲጠየቁ "አሜሪካ ሁሉንም ትቀበላለች ስጋት አይግባችሁ" ሲሉ በተደጋጋሚ ተሰምተው ነበር።



ነገር ግን አሁን ላይ ምንምኳ የቪዛ ችግሩ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ቢሆንም ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው ቃላቸውን ባለመጠበቃቸው ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸው ነው።


ታዲያ በቀጣይስ በዓለም ዋንጫው እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነችው አሜሪካ እና ቃሉን ያልጠበቀው ፊፋ ችግሮችን ይቀርፉ ይሆን ወይስ በታሪክ አስቀያሚው ዓለም ዋንጫ ሆኖ ይመዘገባል? በሒደት የምናየው ይሆናል።




 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

53 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።