Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢቮላ ወረርሽኝ

SM Samuel Mulgeta Jun 4, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 65 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢቮላ ወረርሽኝ

በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ዋልያዎቹ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የሚያደርጉት ጨዋታ መሰረዙ ታውቋል።

 

በመኮነን አልማው!



በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ዳግም ያገረሸው የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ፍርሃትን የቀሰቀሰ ሲሆን በተለይ በአፍሪካ ደግሞ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


ይህ ወረርሽኝ በዘርፉ ላይ የፈጠረውን ጫና ከሀገራችን ጀምረን ስናየው ትላንት አመሻሽ በተሰማ አዲስ ዜና በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ዋልያዎቹ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የሚያደርጉት ጨዋታ መሰረዙ ታውቋል።



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ወደ ሀገረ አሜሪካ አምርቶ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረጉ ይታወሳል።


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በየዓመቱ ቡድኑ ወደ አሜሪካ ተጉዞ ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ የሚታወቅ ሲሆን ዘንድሮም በሐምሌ ወር መጀመሪያ ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ስፍራው ተጉዞ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ቀደም ብሎ ተገልፆ ነበር።

 


ነገር ግን ዋልያዎቹን የሚጋብዘው ዲሲ ዩናይትድ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ሐምሌ 4 እንዲደረግ ታስቦ የነበረው ይህ የወዳጅነት ጨዋታ በምስራቅ አፍሪካ እንደ አዲስ እየተስፋፋ በመጣው የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት እና ቪዛ ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት መረሃ ግብሩ መሰረዙን ገልጿል።


ታዲያ ይህ የወዳጅነት ጨዋታ መሰረዙ ሳይሆን የተሰረዘበት ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።



በእርግጥ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ምንም አይነት በኢቦላ ቫይረስ የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው እንዳልተገኘ ከቀናቶች በፊት ግንቦት 17/ 2018 ዓ.ም ይፋ አድርጎ ነበር።



የዋልያዎቹን የወዳጅነት ጨዋታ መረሃ ግብር የሰረዘው ዲሲ ዩናይትድም በድህረ ገፁ ላይ እንዳለው "ቪዛ ለማግኘት ባለው አስቸጋሪ አሰራር" በማለት ቢሆንም የኢቦላ በሽታ ሌላኛው የጨዋታው መሰረዝ ምክንያት መሆኑንም ግን ገልጾዋል፡፡

 

 
የቪዛው ችግር ቀድሞ የሚጠበቅ እና በሁሉም የስፖርቱ ዘርፍ ላይ ችግር እየፈጠረ የቆየ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን በኢትዮጵያ የሌለውን የኢቦላ በሽታ ምክንያት መደረጉ አነጋጋሪም አስፈሪም ነው።



ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉሪቱ እንዲህ አይነት ውሳኔዎች በተደጋጋሚ ተሰምተዋል።



ታዲያ ይህ ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ የባሰ አስፈሪ ሆኗል።

 

ምክንያቱም ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭት እንደሚያሰጋቸው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት ከቀናት በፊት አስታውቋል።



በዝርዝሩ ደግሞ ኢትዮጵያም ተካታበታለች።



የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት የበላይ ኃላፊ ዣን ካሴያን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ የኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት አለባቸው ተብለው ከተዘረዘሩት 10 ተጨማሪ ሐገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን፣ታንዛንያ ዛምቢያ እና ኬንያ ይገኙባቸዋል።

 

የሆነው ሆኖ ግን ይህ እጅግ ፈጣን ተስፋፊ የሆነው የኢቮላ ወረርሽኝ አፍሪካን እያነፈነፈ እና የጎረቤት ሀገራት አንገት ስር እየተነፈሰ መሆኑ ኢትዮጵያንም እያሸተታት ስለመሆኑ እሙን ነው።



ታዲያ ይህ ነገር ስፖርቱን በተለይም እግር ኳሱ ላይ ከፍተኛ ፈተና የሚያመጣ ስጋት የደቀነ ሲሆን ይህም ከአፍሪካ እግር ኳር ባሻገር 6 ቀናት በኋላ ለሚጀምረው የአለም ዋንጫም አስጊነቱ ከፍ እያለ ነው።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

43 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።