Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የ10 ዓመቱ የሒሳብ ምርመራ እና የግብር ከፋዮች አዲሱ መብት

SM Samuel Mulgeta Jun 5, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 307 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የ10 ዓመቱ የሒሳብ ምርመራ እና የግብር ከፋዮች አዲሱ መብት

የታክስ ስወራን በዘላቂነት ለመከላከል የታቀደው አዲሱ አዋጅ፣ የግብር ባለሥልጣኑ እስከ 10 ዓመት ወደኋላ በመሄድ ኦዲት እንዲያደርግ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን፣ አለመግባባቶችን በገለልተኛ አስማሚ በአጭር ጊዜ ለመፍታት የሚያስችል አሠራርንም አስተዋውቋል።

የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል 10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳብን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀረበ፡፡


ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2018 . ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጁ የታክስ ማጭበርበርን በዘላቂነት ለመከላከል ሲባል የገቢ ሰብሳቢው ባለሥልጣን የታክስ ስወራ መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኘ የግብር ከፋዮችን የሒሳብ ሰነድ እስከ 10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ በድጋሚ የመመርመር (ኦዲት የማድረግ) እና ተጨማሪ ግብር የማስከፈል ሰፊ ሥልጣን የሚሰጥ ነው።


በዚህ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ማሻሻያ ረቂቅአንቀጽ 28” ላይ እንደተደነገገው ባለሥልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኘ የታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት የይርጋ ጊዜ ውስጥ የታክስ ስሌቱን በድጋሚ ኦዲት በማድረግ ሊያሻሽል ይችላል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

 

gebiwoch


ይህ 10 ዓመት ገደብ ሊቀመጥ የቻለው በኢትዮጵያ የንግድ ሕግና የሒሳብ አያያዝ ሕጎች መሠረት የሒሳብ ሰነዶች ተጠብቀው መቆየት ያለባቸው 10 ዓመታት ብቻ በመሆኑ ሲሆን ተራ ስህተቶች ባሉበት መደበኛ ሁኔታ ግን የይርጋ ጊዜው 5 (አምስት) ዓመት ብቻ ሆኖ እንዲቀጥል ተደንግጓል።



ረቂቅ አዋጁ የሀገሪቱን የታክስ ስወራ ለመግታት ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ ሲሆን በተለይም ደረሰኝ ባለመቁረጥ በሚፈጸሙ ግብይቶች ላይ ከባድ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን ጥሏል።



ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያ በሰጠው ማሳሰቢያ "የሀገር ውስጥ የታክስ እና ታክስ ያልሆኑ ገቢዎችን የመሰብሰብ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከር ያስፈልጋል" ማለቱ መንግሥት አዋጁን ይዞ ለመቅረቡ ትልቅ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ይታመናል።



በሌላ በኩል ረቂቅ አዋጁ በዚህ የቁጥጥርና የኦዲት ሂደት ውስጥ በታክስ ባለሥልጣኑ እና በታክስ ከፋዩ መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በአጭር ጊዜ ለመፍታት የሚያስችል አዲስ "የመስማማት ሥርዓት" በገለልተኛ አስማሚ አማካኝነት ስራ ላይ እንዲውል ይፈቅዳል።



ቀደም ሲል በነበረው ሕግ ግብር ከፋዮች የተጣለባቸውን ተጨማሪ ግብር ለመቃወም ቅድሚያ ከተወሰነባቸው የገንዘብ መጠን 50 እስከ 75 በመቶ የሚሆነውን ከፍለው ለቅሬታ ሰሚ ለግብር ይግባኝ ኮሚሽን እና በየደረጃው ላሉ ፍርድ ቤቶች ማቅረብ የሚችሉ ቢሆንም ሂደቱ ግን መፍትሔ ለመስጠት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ነበር።

 

አዲሱ አሠራር ግን የቀደመው መደበኛ ሂደት እንዳለ ሆኖ አለመግባባቶችን በሚስጥራዊነት መርህ ላይ በመመስረት በገለልተኛ አስማሚ አማካኝነት በፍጥነትና በአጭር ጊዜ ለመፍታት ትልቅ ዕድል እንደሚሰጥ በረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ ላይ ተመላክቷል።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

45 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።