Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዜጎቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ከስምምነት ላይ ደረሰ

SM Samuel Mulgeta May 31, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 162 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዜጎቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ከስምምነት ላይ ደረሰ

የኢትዮጵያ መንግስት ስለዚሁ ጉዳይ ለመወያየት ወደ ደቡብ አፍሪካ ልዑክ ልኮ ነበር፡፡

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለውመጤ ጠልእንቅስቃሴ ሳቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት፣ የንብረት ዘረፋ እና የስራ ክልከላ ለመከላከል የኢትዮጵያ መንግስት የላከው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ጋር በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል።

 

የልዑካን ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ግንኙነትና ትብብር ዲፓርትመንት፣ የድንበር አስተዳደር፣ የፖሊስ አገልግሎት እና የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ተወካዮች ጋር ያደረገው ውይይት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

የዜጎች ደህንነት ዋስትና፦ ሁለቱ አካላት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን (ሕጋዊ ሰነድ ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው) የደህንነት ዋስትና እንዲኖራቸው መስማማታቸውን ተከትሎ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥረት ይደረጋል።

 

የሕግ የበላይነትና አያያዝ፦ ማንኛውም ሕገ-ወጥነት በሕገ-ወጥ መንገድ መፈታት እንደሌለበት የተሰመረበት ሲሆን፣ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎችም ቢሆኑ በደቡብ አፍሪካ ሕግና በአገሪቱ ተቀባይነት ባላቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ብቻ እንዲስተናገዱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

 

 

የወንጀል ሰንሰለቶችን መቆጣጠር፦ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ሌሎች ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ የተቀናጀና ማያዳግም የሕግ እርምጃ ለመውሰድ ተስማምተዋል። በወንጀል ተግባራት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያመልጥ በግልጽ ተቀምጧል።

 

የኢትዮጵያ መንግስት ሚና፦ በሂደቱ ለሚኖሩ የትብብርና ቅንጅት ስራዎች የኢትዮጵያ መንግስት በኤምባሲው እና በሌሎች ተቋማት አማካኝነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

 

የዜጎች ሀላፊነትና የጋራ ተጠቃሚነት፦ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተደራጅተውና ተቀናጅተው መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው፣ የአገሪቱን ሕግ ማክበርና ከወንጀል ድርጊቶች መራቅ እንደሚገባቸው ተገልጿል። በተናጥል ከመንቀሳቀስ ይልቅ ኃብትን በማሰባሰብ ወደ ኩባንያና ትላልቅ ኢንቨስትመንቶች በማደግ በደቡብ አፍሪካም ሆነ በትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ በመስራት የጋራ ተጠቃሚነትን መፍጠር እንደሚቻል መፍትሄ ሆኖ ቀርቧል።

 

በመጨረሻም፣ የተፈጠሩትን ውጥረቶች ለመቀነስ እና ለዜጎች የተረጋጋ የኑሮና የሥራ ከባቢ ለመፍጠር፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በመንቀሳቀስ የራሳቸውንና የአገራቸውን ጥቅም እንዲያስጠብቁ በልዑካን ቡድኑ በአጽንዖት ተገልጿል።

 

በአጠቃላይ የልዑካን ቡድኑ ያደረገው ውይይት፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ረገድ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት የተመዘገበበት ነው። ይህ ስምምነት የሁለቱን አገራት የረዥም ጊዜ ግንኙነት ከማጠናከሩ ባሻገር፣ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቀልበስ የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ፈጥሯል።ኢትዮጵያ

 

ይሁን እንጂ የዚህ ስምምነት ውጤታማነት የሚለካው በሁለቱም ወገኖች የጋራ ቁርጠኝነትና የዜጎች ተገዢነት ነው።

 

ኢትዮጵያውያን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ተደራጅተው መንቀሳቀሳቸው፣ ከወንጀል ተግባራት መራቃቸው እና በትውልድ አገራቸውም ሆነ በደቡብ አፍሪካ ኢንቨስትመንት ውስጥ በጋራ መሳተፋቸው፣ ውጥረቱን በዘላቂነት ከመፍታት ባለፈ ለሁለቱም አገራት ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅምን የሚሰጥ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

34 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።