Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

እመ-ዓዕላፍ የታሪክ መልኮች ያሉት የዓለማችን ወደር አልባው ደርቢ – ኤልክላሲኮ

A Administrator May 14, 2026 Updated 3h ago 4 ደቂቃ ንባብ 40 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
እመ-ዓዕላፍ የታሪክ መልኮች ያሉት የዓለማችን ወደር አልባው ደርቢ – ኤልክላሲኮ

በ35ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ባርሴሎናን ከሪያል ማድሪድ ያገናኛል፡፡

ባርሴሎና በውድድር አመቱ 88 ነጥቦችን በመሠብሰብ ሊጉን ከተከታዩ እና ከምሽቱ ተጋጣሚው ሪያል ማድሪድ በ11 ነጥብ እርቆ እየመራ ይገኛል፡፡

የካታላኑ ክለብ በምሽቱ ጨዋታ የማይሸነፍ ከሆነ ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩት ለተከታታይ ሁለት አመት የላሊጋው ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

Advertisement
Your ad could be here — contact us

በላሊጋው ብቻ ያለፉትን አስር ጨዋታዎች ድል እያደረገ የመጣው ባርሴሎና ዛሬም አሸናፊ ከሆነ  ወይም አቻ ከወጣ ሻምፒዮን መሆኑን ሲያረጋግጥ ሎስብላንኮቹ በበኩላቸው ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት ያለምንም ዋንጫ አመቱን ያጠናቅቃሉ።

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ባርሴሎና አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ሪያል ማድሪድ በአንዱ ድል አድርጓል፡፡

ከአራት አምስት አመታት በፊት እጅግ በከፍተኛ ጉጉት ይጠበቅ የነበረውና እልህ አስጨራሽ ፉክክር የሚታይበት ኤልክላሲኮ ከቅርብ አመታት ወዲህ ድምቀቱን እያጣ መጥቷል፡፡

የኤልክላሲኮን ታሪክ ወደኋላ ተመልሰን ከጅምሩ ስንመለከት የመጀመሪያው የደርቢ ጨዋታ የተደረገው እ.ኤ.አ በ1902 ሲሆን በ124 አመታትን አስቆጥሯል።

እነዚህ ሁለቱ የአለማችን ኃያላን ክለቦች እርስ በእርስ መጫዎት ከጀመሩበት እ.ኤ.አ 1902 ጀምሮ 124 አመታት ውስጥ በድምሩ 263 ግጥሚያዎችን አድርገዋል።

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉትን ጨዋታ ባርሴሎና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ግጥሚያዎች ግን ሪያል ማድሪድ አሸነፈ 106 ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ነው። የካታሎኑ ክለብ ቤርሴሎና በበኩሉ በአንድ ድል ተበልጦ 105 ጊዜ የረታ ሲሆን በ52 ግጥሚያዎች አቻ ተለያይተዋል።

ዛሬ ባርሴሎና በሜዳው የሚያደርገውን ይህንን ተጠባቂ የኤልክላሲኮ ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ አንድም ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል ፣ አንድም የእርስ በርስ ግጥሚያ ላይ የተወሰደበትን የድል ብልጫ የሚጋራ ይሆናል።

በሁለቱ ክለቦች የእርስ በርስ 126 ግጥሚያዎች ላይ በድምሩ 883 ግቦች ሲመዘገቡ ባርሴሎን 436 ፣ ሪያል ማድሪድ ደግሞ 447 ግቦችን  አስቆጥረዋል ።

ዛሬ በሚጫዎቱበት የላሊጋው መድረክ ብቻ 191 ጨዋታዎችን ያደረጉት ሁለቱ ክለቦች ተቀራራቢ ታሪክ አላቸው።
ሆኖም ሪያል ማድሪድ 80 ድሎችን በማስመዝገብ የበላይ ነው።
ባርሴሎና በበኩሉ 76 ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ35 ግጥሚያዎች አቻ ተለያይተዋል። በግብ ብዛትም በተመሳሳይ ተቀራራቢ ቁጥር የሚጋሩ ሲሆን ካታላኖቹ 309 ፣ ሎስ ብላንኮቹ ደግሞ 310 ግቦችን አስቆጥረዋል።

በኤልክላሲኮ ታሪክ በላሊጋው ብቻ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎችን ስንመለከት አርጄንቲናዊዉ እና የአለም ዋንጫው አሸናፊ ሊዮኔል አድሬስ ሜሲ ቀዳሚ ነው።
የአለማችን ምርጡ ተጨዋች እንደሆነ ቁጥሮች እና ብዙ ሰዎች የሚመሰክሩለት ሊዮኔል መሲ በ29 የኤልክላሲኮ ጨዋታዎች 18 ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ሲሆን ፣ ከእሱ በመቀጠልም ሌላኛው አርጀንቲናዊ እና የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ አልፍሬዶ ዲ ስቴፋኖ በ14 ግቦች ይከተላል።
በተጨማሪም የዓለማችን ቀዳሚው ደርቢ እንደሆነ በሚታመንበት በዚህ የኤልክላሲኮ ጨዋታ ኩሌ ሴሳር ሮድሪጌዝ 12 ፣ ራውል ጎንዛሌዝ 11 እና
ክርስቲያኖ ሮናልዶ 9 ግቦችን አስመዝግበዋል።

በሁሉም መድረክ በተደረጉ አጠቃላይ የሁለቱ ክለቦች ደርቢ ጨዋታ ላይም ሊዮኔ ሜሲ ፊት አውራሪ ነው።
የ8 ጊዜ ባላንዶር አሸናፊው ሊዮኔል መሲ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባደረጋቸው 45 የኤልክላሲኮ ጨዋታዎች ላይ 26 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከእሱ ቀጥሎ በአጠቃላይ 18 ጎሎችን በማስቆጠር የሎስብላንኮቹ የቀድሞ ኮከብ አልፍሬዶ ዲ ስቴፋኖ እና ክሪስቲያ ሮናልዶ ይከተላሉ።

የአለማችን ታላቅ ስለሆነው ደርቢ (ኤልክላሲኮ) ሲነሳ አብሮ የሚነሳ አንድ ነገር አለ። እርሱም የእግርኳስ ባለዉለታዎቹ ሊዮኔል መሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ናቸው።  እኒህ ሁለቱ የአለማችን እግር ኳስ ፈርቀዳጆች ከ2009–2018 ድረስ ለ9 አመታት የነበራቸው ፍጥጫ አለም ለሁለት የከፈለም ፣ ላሊጋውን ላይ የሰቀለ እና እና የእግር ኳስ አይኖችን ሁሉ ወደ ስፔን እንዲመለከቱ ያደረገ ነበር።

እነዚህ የእግር ኳስ ኮከቦች በላሊጋው በነበራቸው የ9 አመታት ጫፍ የነካ ፉክክር ኤልክላሲኮ ደርቢነሰ ወደሌላ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነበር።
ሁለቱም ተጫዋቾች በባላንዶር ሽልማት ጭምር የሚፎካከሩ የክለባቸው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ከመሆናቸውም 
የክለቦቻቸውንና የሊጉን ብዙ ሪከርዶች ሰባብረዋል።
በነበራቸው ጊዜ የአውሮፓ የወርቅ ጫማን ሮናልዶ ሶስት ጊዜ ፤ ሜሲ ደግሞ አምስት ጊዜ አሸንፏል። በተጨማሪም ሜሲ አምስት ጊዜ ፣ ሮናልዶ ደግሞ አራት ጊዜ ባላንዶርን አሸንፈው ታሪክ በመስራት ሪከርድ ሰብረዋል።

በክለቦቹ መካከል የተመዘገቡ ሪከርዶችን እንመልከት…

በተከታታይ ድል…
ሪያል ማድሪዶች እ.ኤ.አ ከ1962 ጀምሮ እስከ 1965 ድረስ በሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ባርሴሎናን በማሸነፍ በኤልክላሲኮ ታሪክ ረጅም የማሸነፍ ክብረወሰን ባለቤት ናቸው፡፡

በአንድ ጨዋታ የተመዘገበ ሰፊ የግብ ልዩነት…
እ.ኤ.አ በ1943 ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን 11 ለ 1 ያሸነፈበት የኮፓ ዴል ሬይ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በኤልክላሲኮ ታሪክ የተመዘገበ ሰፊ የግብ ልዩነት ነው፡፡

ባሳለፍነው 2024/25 የውድድር ዓመት ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር በተገናኙባቸው አጋጣሚዎች ደግሞ የባርሴሎና የበላይነት ተመዝግቧል፡፡

የውድድር አመቱ የመጨረሻው እና በታሪክ 264ተኛዉ የኤልክላሲኮ ተጠባቂ ፍልሚያ ደግሞ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኑ-ካምፕ ኑ ስቴዲየም ይደረጋል።

የውድድር አመቱ የመጀመሪያው የኤልክላሲኮ ግጥሚያ ከወራቶች በፊት በበርናቮው የተደረገ ሲሆን ሪያል ማድሪድ 2-1 ማሸነፉ ይታወሳል።

ዛሬስ?… የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በሁከት እና ብጥብጥ ችግር ውስጥ የሚገኘውን ተቀናቃኙን ክለብ በማሸነፍ የድል ታሪኩንም ተጋርቶ ፣ ሻምፒዮንነቱንም አረጋግጦ በአንድ ደንጋይ ሁለት ወፍ ይመታል?… ወይስ ማድሪድስታዎች እጅ ባለመስጠት ታሪካዊ ክብራቸውን ያስጠብቃሉ?

A
ስለ ጸሐፊው

Administrator

12 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።