Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው ሰው ሰራሽ አስተውሎት

SM Samuel Mulgeta Jun 5, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 241 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው ሰው ሰራሽ አስተውሎት

መተግሪያው መምህራን በተለመዱ የዕለት ተዕለት የቢሮክራሲ ተግባራት የሚያጠፉትን ውድ ጊዜ ያስቀርላቸዋል የተባለ ሲሆን ከተማሪዎቻቸው ጋር ቀጥታ ለሚኖራቸው ግንኙነት በቂ ጊዜ እንዲያገኙም እንደሚያደርጋቸው ተጠቁሟል፡፡

ለመምህራን የትምህርት እቅድ የሚያዘጋጅ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን የሚያመነጭ እንዲሁም የማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ የሚያቀናጅ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ተበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ መዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

ኤጀንቲክ መምህር ረዳትየተሰኘው መተግበርያው የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የዕለት ተዕለት የሥራ ጫና በእጅጉ የሚቀንስ እና ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት ራሱን ችሎ ተግባራትን ማከናወን የሚችል ነው።

Advertisement
Your ad could be here — contact us



ይህ መተግበሪያ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ ቴክኖሎጂ ላይ ከመተማመን ይልቅ በኮምፒውተር ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሰራና በውስጥ አቅም የበለጸገ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።



መተግበሪያው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት 9 እስከ 12 ክፍል ያሉትን መጽሃፍቶች በሙሉ ዳታሴት በማድረግ መጻሕፍቱን ሙሉ በሙሉ እንዲመረምርና እንዲገነዘብ ተደርጎ የተዘጋጀ ቀላል ሞዴል ሲሆን ምንም ዓይነት ከፍተኛ የሃርድዌር ዝርዝር ሳይጠይቅ በቀላሉ በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ መሥራት መቻሉ ልዩ ያደርገዋል።

 


ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያ በርካታ ተግባራትን ማከናወን የሚችል ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የትምህርት እቅድ ማዘጋጀት፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ማመንጨት፣ እንዲሁም የማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ ማቀናጀት የሚችል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

 

 

ይህም መምህራን በተለመዱ የዕለት ተዕለት የቢሮክራሲ ተግባራት የሚያጠፉትን ውድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የሚያስቀርላቸው ሲሆን ከተማሪዎቻቸው ጋር ቀጥታ ለሚኖራቸው ግንኙነት በቂ ጊዜ እንዲያገኙና የማስተማር ብቃታቸውን በማጎልበት የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

 


ይህ መተግበሪያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያካሂደው አጠቃላይ የትምህርት ዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ አካል መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ በኦፍላይን የሚሰራ መሆኑ የኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለምንም መቆራረጥ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።

 

 

ይህም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የትምህርት ጥራት ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ለማጥበብ የሚያስችል ይሆናል።

 

 

 

በዚህም ተማሪዎች በተከታታይ ምዘና የተሻለ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ውጤታቸውን ያሻሽላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማስገኘቱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

 

 

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ መምህራንና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ ነው የተገለጸው።

 

 

በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው የዚህ መተግበሪያ ቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰውየኢትዮጵያ የትምህርት ለውጥ ኦፕሬሽንፕሮጀክት ድጋፍ እየተከናወነ እንደሚገኝ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

45 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።