Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አለም አቀፍ ትንታኔ

ደቡብ ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለመከታተል የተቋቋመውን የግብፅ ምሽግ ዘጋች

SM Samuel Mulgeta May 31, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 163 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ደቡብ ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለመከታተል የተቋቋመውን የግብፅ ምሽግ ዘጋች

ይህ ወታደራዊ ምሽግ በመዘጋቱ ግብፅ የህዳሴውን ግድብ እንቅስቃሴን ለመከታተል የነበራትን አማራጭ ያሳጣታል ተብሏል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ እና በላይኛው ናይል ግዛት ፓጆክ  አካባቢ ግብፅ መስርታው የነበረውን ድብቅ ወታደራዊ ምሽግ በአስቸኳይ እንዲዘጋ ማዘዙን የዓረብኛ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

 

ይህ ውሳኔ ግብፅ በናይል ተፋሰስ ላይ ያላትን ጥቅምና ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ለማስጠበቅ በምትታገልበት፣ የኢትዮጵያ ቀጠናዊ ተፅዕኖ እያደገ በመጣበትና በሱዳን ጦርነት ሳቢያ የቀጠናው የኃይል አሰላለፍ እየተቀያየረ ባለበት ወቅት የተወሰነ ነው።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


ይህ ደቡብ ሱዳን እንዲዘጋ ያዘዘችው ተቋም የቴክኒክ ድጋፍ፣ ወታደራዊ ሥልጠና፣ የላቀ የደኅንነት ክትትል እና የሎጅስቲክስ ቅንጅት ሥራዎችን የሚያከናውን 260 የሚያህል የሰው ኃይል ነበረው ተቋም ነው።


የደቡብ ሱዳን መንግሥት ይህንን ውሳኔ ለመወሰን ከበቃባቸው ምክያቶች አንዱ ሀገሪቷ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ የግብፅን የቆየ የታችኛው ተፋሰስ የውሃ መብት ተሟጋችነት አቋም በመጣስ የናይልን ውሃ በድጋሚ ለመጋራት ከሚፈልጉት የላይኛው ተፋሰስ አገራት ጎን ለመቆም በመወሰኗ ነው።

 
በሁለተኝነት በሱዳን ባለው ጦርነት ምክንያት  የነዳጅ መሠረተ ልማቶች በመውደማቸው ጁባ አዳዲስ አማራጮችን ለመፈለግ ወደ አዲስ አበባ በመጠጋቷ ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት ውስጥ መግባት አለመፈለጓ ተጠቅሷል።

 
በሌላ በኩል በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል እየተባባሰ ባለው ውጥረት ውስጥ የደቡብ ሱዳን እጅ እንዳይገባ ያላት ስጋት ሌላኛው ምክንያት ነው።


በተጨማሪም የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ይህንን ውሳኔ የወሰኑት በተቀናቃኞቻቸውና በአጋሮቻቸው ፊት የአገሪቱን ጠንካራ የሉዓላዊነት ስልጣን ለማሳየት ነው ተብሏል።

 
በዚህም ይህ ወታደራዊ ምሽግ በመዘጋቱ ግብፅ የህዳሴውን ግድብ እንቅስቃሴን ለመከታተል የነበራትን አማራጭ ያሳጣታል ተብሏል። 

 

ነገር ግን ወደፊት በሚደረጉ የቀይ ባሕር ደኅንነት ዝግጅቶች ላይ ኢትዮጵያን ለማግለል፣ ከኤርትራ ጋር ያላትን ጥምረት ለማጠናከር፣ የሶማሊያን ግዛታዊ አንድነት ለመጠበቅ እና ከሱዳን መደበኛ ጦር ጋር ያላትን ቅንጅት ለማጠናከር እየሠራች መቀጠሏ አይቀሬ እንደሆነም ተገምቷል።

 

በአሁኑ ወቅት በካይሮ እና በአዲስ አበባ በኩል በሶማሊያ፣ በኤርትራ፣ በጅቡቲ እና በኡጋንዳ እየታየ ያለው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እና የደኅንነት እንቅስቃሴ ቀጠናው ወደ አዲስ የኃይል አሰላለፍ እና ስትራቴጂካዊ ሽኩቻ ምዕራፍ እየገባ መሆኑን ያሳያል።

 
በአጠቃላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ውሳኔ የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ተፅዕኖ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ግብፅ በቀጠናው ያላትን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለመጠበቅ የምታደርገውን ጥረት አዲስ ፈተና ውስጥ የጣለ ነው።
 

ይሁን እንጂ የዚህ ውሳኔ ዘላቂ ውጤታማነት የሚለካው በደቡብ ሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል በሚኖረው የኢኮኖሚና የደኅንነት ትብብር ጥንካሬ ላይ ነው።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

34 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።