Home / ዜና / የዕለት ዜና / በሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ የሚገኝ የግብፅ ጦር በሱዳን አማፂያን ተከበበ

በሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ የሚገኝ የግብፅ ጦር በሱዳን አማፂያን ተከበበ

መጋቢት 23/2018 (ገበያ ሚዲያ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ በሚገኘው የሱዳን ግዛት ውስጥ የሰፈረ አንድ የግብፅ ጦር ሻለቃ “ታሲስ” ( ተብሎ በሚጠራው የሱዳን መስራች ጥምረት ኃይሎች መከበቡ ተሰምቷል።

በሱዳን ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች እና በአብዱልዓዚዝ አል-ሒሉ በሚመራው የሱዳን ሕዝባዊ ነፃነት ንቅናቄ ሰሜን የሚመራው ይኸው ጥምረት በሰማያዊ አባይ ግዛት በሳሊ አካባቢ የሚገኘውን የግብፅ ጦር ሙሉ በሙሉ ከቦታል።

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ተከቦ የሚገኘው የግብፅ ጦር ክፍል 640 ያህል መኮንኖችና ወታደሮችን የያዘ ነው።

በክበባ ውስጥ የሚገኙት የግብፅ መኮንኖች ከሳሊ ተነስተው ወደ ግዛቱ ዋና ከተማ ዳማዚን በሰላም ለመውጣት ድርድር ቢጀምሩም የጥምረቱ ኃይሎች ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ጦሩ በአስቸኳይ እጁን እንዲሰጥ መጠየቃቸው ታውቋል።

ይህ የግብፅ ጦር ቀደም ሲል በጄኔራል አል-ቡርሃን ለሚመራው የሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) ድጋፍ ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ቆይቶ ግን እንቅስቃሴው ወደ ወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ተግባራት መዞሩ ተመላክቷል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት የግብፅ ጦር ክፍሉ በሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ በሚገኘው የሱዳን ግዛት ውስጥ እንዲሰፍር የፈቀደለት የጄኔራል አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) ነው።

በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም የግብፅ ጦር በቀጣይ ስለሚወስደው እርምጃ እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *