Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አለም አቀፍ ትንታኔ

ግብጽ በአፍሪካ ያላት ተጽዕኖ እየቀነሰ መምጣቱን ሪፖርት አመላከተ!

SM Samuel Mulgeta Jun 6, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 243 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ግብጽ በአፍሪካ ያላት ተጽዕኖ እየቀነሰ መምጣቱን ሪፖርት አመላከተ!

ለዚህ እንደ ምክንያትነት የቀረበው የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ እና ተመርቆ ሥራ መጀመሩን ተከትሎ ነው።

በአንድ ወቅት የግብፅን ብሔራዊ ጥቅሞች ወደ ዓለም የጋራ አጀንዳነት ይቀይር የነበረው የአረብ ብሔረተኝነት ሥርዓት መዳከሙ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር በናይል ተፋሰስ እና በአፍሪካ ቀንድ ለምታደርገው ሰፊ የዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ ዕድል መክፈቱን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባወጣው አዲስ ትንተና አስታውቋል።


ግብፅ አሁንም የስዊዝ ቦይ፣ ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል እና የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምድ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ብትሆንም ቀደም ሲል የናይል ወንዝ የደኅንነት ሥጋቷን እንደ አጠቃላይ የአረብ ዓለም የጋራ አደጋ አድርጋ የማቅረብ አቅሟ ግን አሁን ላይ በእጅጉ ቀንሷል።



ይህም ግብፅ የኢትዮጵያን የናይል ተፋሰስ የልማት እንቅስቃሴ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመጫን ወይም ለማደናቀፍ የምታደርገውን ጥረት በእጅጉ አዳክሞባታል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


እንደ ትንተናው ማብራሪያ ይህ የኃይል ሚዛን ሽግግር በይፋ የታየው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ እና ተመርቆ ሥራ መጀመሩን ተከትሎ ነው።



ግብፅ ግድቡን የአረብ ደኅንነት ሥጋት አድርጋ ለማሳየትና የአረብ ሊግን በማንቀሳቀስ ኢትዮጵያን ለማግለል ለዓመታት ብትጥርም በምድር ላይ የተፈጠረው አዲስ እውነታ ግን የአረብ ሊግ መግለጫዎች ብቻ የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ሊያስቆሙ እንደማይችሉ አረጋግጧል።


ይህ የግብፅ የጫና አቅም መላላት በአፍሪካ ቀንድም በግልጽ እየታየ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፣ኳታር፣ ቱርክ እና ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ያላቸውን ፖሊሲ በቀላሉ ከግብፅ የናይል አጀንዳ ጋር አያያዙም።



ይልቁንም ፖሊሲዎቻቸው የተቀረጹት በራሳቸው የኢኮኖሚ፣ የወደብ፣ የኢንቨስትመንት እና የሎጂስቲክስ ጥቅሞች ላይ ተመስርቶ በመሆኑ ኢትዮጵያ ከአሁን በኋላ አንድ ወጥ የሆነ ፀረ-ኢትዮጵያ የአረብ ጎራ እየገጠማት እንዳልሆነ ተጠቅሷል።



በሌላ በኩል በቀይ ባሕር ቀጣና ግብፅ የምትከተለው የባሕር ዳርቻ አገራትን ብቻ ያካተተ ጠባብ የደኅንነት እይታም ፈተና እየገጠመው ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሰፊ የሕዝብ ቁጥር፣ የኢኮኖሚ ክብደት እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ሀገር በቀይ ባሕር የደኅንነት ውይይቶች ውስጥ ሊገለል እንደማይገባ ትንተናው ያመለክታል።



በተለይም ... 2024 እና 2025 በቀይ ባሕር በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት የግብፅ የስዊዝ ቦይ ወርሃዊ ገቢ ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ መውረዱ የባሕር መተላለፊያውን ደኅንነት በጠባብ ቅንጅት ብቻ ማስተዳደር እንደማይቻል ማረጋገጫ ሆኗል።



ይህ የተፈጠረው ስትራቴጂካዊ ዕድል ኢትዮጵያ እያንዳንዱን ግንኙነቷን በግብፅ ዕቅድ ሳታሳልፍ ራሷን እንደ ትልቅ የአፍሪካ ገበያ፣ የኃይል አምራች እና የሎጂስቲክስ አጋር አድርጋ እንድታቀርብ በር ከፍቶላታል።

 

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ይህንን ዲፕሎማሲያዊ ምኅዳር በሌላ የውጭ ኃይል ጥገኝነት እንዳትተካው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባት ተመላክቷል።


በመጨረሻም ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የባሕር ላይ አጀንዳና የናይል ልማት ፍላጎት በማንኛውም አገር ላይ እንደ ተቃራኒ እርምጃ ሳይሆን ሁሉንም ያካተተ ሕጋዊና ከጋራ የኢኮኖሚ ጥቅም ጋር የተገናኘ መረጋጋት የመፍጠር ዓላማ አድርጋ በግልጽ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ልታቀርብ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባወጣው ትንተና አሳስቧል።

 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

47 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።