Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ መመሪያ ምን ነገሮችን ይዟል?

SM Samuel Mulgeta May 30, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 191 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ መመሪያ ምን ነገሮችን ይዟል?

ደንቦቹን በመተላለፍ የተሳሳተ መግለጫ መስጠት ወይም የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማለፍ መሞከር በገንዘብ ቅጣት፣ በንብረት መውረስ አልፎ ተርፎም በወንጀል ተጠያቂነት ያስቀጣል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከግንቦት 21 ቀን 2018 . ጀምሮ ተግባራዊ የሆነውን አዲሱን የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ ይፋ አድርጓል።

 

መመሪያው በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ ጫና ሳያሳድሩ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥና ቀደም ሲል የነበሩ የቁጥጥር ክፍተቶችን በመድፈን ግልጽነትን ለማስፈን ያለመ ነው ተብሏ።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

አዲሱ አሠራር በሁሉም የፍራንኮ ቫሉታ ግብይቶች ላይ የጉምሩክ ኮሚሽንን "FEMoUS" ዲጂታል ሥርዓት መጠቀምን የግዴታ አድርጓል። ማንኛውም አስመጪ ለሚያስገባቸው ዕቃዎች ትክክለኛ የባለቤትነት ማረጋገጫ እና የምንዛሬ ምንጭ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

 

በመመሪያው ውስጥ በተካተተው ሰንጠረዥ መሠረት ተጠቃሚዎች ማቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ሰነዶች እንደሚከተለው ተለይተዋል፦

 

ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የኤምባሲ ወይም ተገቢው የመንግስት መስሪያ ቤት ማረጋገጫ።

 

ኢንቨስተሮችና ማኑፋክቸሪንግ፦ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እና ለስራው አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ።

 

በቋሚነት ወደ ሀገር የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን፦ የቋሚ መመለሻ ማረጋገጫ እና በውጭ ሀገር ሲሰሩበት የነበረውን የስራ ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ።

 

የሃይማኖት፣ የትምህርትና ሙያዊ ተቋማት፦ ለታሰበው ስራ የሚመጥኑ መሆኑን የሚያሳይ የስጦታ ወይም የእርዳታ የምስክር ወረቀት።

 

የግል ስጦታና የጥናት መሣሪያዎች፦ በቀጥታ ለተፈቀደላቸው ስራ መዋላቸውን የሚያረጋግጥ ደጋፊ ሰነድ።

 

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ግለሰቦች፦ የመኖሪያ ፈቃድ (እስከ 5,000 ዶላር ነጻ ዕቃ ለማስገባት)

 

ስፖርትና ስነ-ጥበብ፦ ሽልማት ሰጪው አካል የሚሰጠው የሽልማት ማረጋገጫ (ከንግድ ዓላማ ውጭ መሆኑን የሚያሳይ)

 

ኤክስፖርትና የንግድ ናሙናዎች፦ የንግድ ሚኒስቴር ማረጋገጫ እና ከንግድ ስራው ጋር ያላቸው ግንኙነት በሰነድ የተረጋገጠ።

 

ኮንቴይነሮችና ተመላሽ ማሸጊያዎች፦ ለቀረቡት ዋና ዕቃዎች የቀረቡ ሰነዶች እንደ ደጋፊ ማስረጃ።

 

አካል ጉዳተኞች፦ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ልዩ መሣሪያዎች ማረጋገጫ።

 

ለጤና ችግር የሚውሉ መድሃኒቶች፦ የህክምና ማረጋገጫ (ምንም አይነት የዋጋ ገደብ የሌለበት)

 

ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፦ እንደ ጉዳቱ መጠን እና አይነት የተወሰነ ማረጋገጫ።

 

ለአስቸኳይ ስራ የሚተኩ ዋስትናዎች፦ የጠፉ ወይም የተበላሹ ዕቃዎች መሆናቸውን የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ።

 

መመሪያው የህግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ ጥብቅ እርምጃዎችን አስቀምጧል። ደንቦቹን በመተላለፍ የተሳሳተ መግለጫ መስጠት ወይም የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማለፍ መሞከር በገንዘብ ቅጣት፣ በንብረት መውረስ አልፎ ተርፎም በወንጀል ተጠያቂነት ያስቀጣል።

 

የንግድ ፈቃድ እስከመነጠቅ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃም ሊወሰድ ይችላል።

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሠራሩን ለማዘመን እና ለሕገ-ወጥ ግብይቶች ምንም አይነት ቦታ እንደሌለ ለማሳወቅ ይህንን ጥብቅ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። ሕግ አክባሪ የሆኑ ነጋዴዎች አዲሱን አሠራር በመከተል ከሕግ ጣጣ በራቀ መልኩ የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያከናውኑ ባንኩ አሳስቧል።

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

32 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።