Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

SM Samuel Mulgeta May 28, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 412 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

ከመካከለኛው ምስራቅ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ለጥቂት ጊዜያት አባርቶ የቆየው ጦርነት አሁን ላይ መልኩን በመቀየር ወደ ቀጥተኛ ጥቃቶች ተሸጋግሯል።

 

የአሜሪካ ጦር ስልታዊ በሆነችው የኢራን የወደብ ከተማ ባንዳር አባስ አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ይዞታ ላይ አዲስ እና ድንገተኛ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በኩዌት በሚገኝ የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የሚሳይል እና የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን ይፋ አድርጓል።



ይህ ማለት ደግሞ አሁን ላይ ሁለቱ ሀገራት በቀጥታ ሚሳይል ወደ መተኮስ መሸጋገራቸውን ያሳየ ሲሆን ይህም ለአካባቢው ቀጠናዊ መረጋጋት እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ከፋች ሆኗል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us



አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ስትሰነዝር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከሁለት ቀናት በፊትም በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ የሚሳኤል ቤዞች እና ፈንጅ ሲቀብሩ ነበር ባለቻቸው ጀልባዎች ላይ ተመሳሳይ የአየር ድብደባ መፈጸሟ ይታወሳል።



የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በበኩሉ የተወሰደው እርምጃ በሆርሙዝ ሰርጥ ዓለም አቀፍ የባህር ትራፊክ ላይ ስጋት ፈጥረዋል የተባሉ አራት የኢራን ድሮኖችን ለማውደም የታለመ የቅድመ መከላከል ስትራቴጂ መሆኑን ገልጿል።



ይህ ወታደራዊ አሰላለፍ በመሬት ላይ ካለው ተጨባጭ የዲፕሎማሲ ጥረት እውነታ ጋር ፍጹም የሚጋጭ ሲሆን በተለይም ዋሽንግተን እና ቴህራን ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ይጀምሩታል ተብሎ ይገመት የነበረውን የሰላም ድርድር ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ የጣለ ነው በመባል ወቀሳ እየቀረበበት ይገኛል።



አብዮታዊ ዘቡ በበኩሉ ለአሜሪካ ትንኮሳ የተሰጠው ምላሽ የመጀመሪያው ማስጠንቀቂያ ብቻ መሆኑን በመግለጽ "ዋሽንግተን ጠብ አጫሪነቷን የምትቀጥል ከሆነ የላቀ እና የበለጠ ወሳኝ እርምጃ ይጠብቃታል" ሲል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

 

Iran says it targeted US airbase after fresh American strikes near Bandar  Abbas



በሌላ በኩል በጥቃቱ ወቅት በኩዌት የአደጋ ጊዜ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የኩዌት ጦር ግን የአየር መከላከያ ሥርዓቱ ወደ አየር ክልሉ የገቡ የጠላት ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአየር ላይ እየጠለፈ ሲከላከል እንደነበር አስታውቆ ፍንዳታዎቹ በትክክል ከየት አቅጣጫ እንደመጡ ከመግለጽ ተቆጥቧል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ እና የኢራን ፍጥጫ በዚህ መልኩ በሆነበት ሰዓት የእስራኤል እና የሊባኖስ ግንባርም ወደ ከፋ ሰብአዊ ጥፋት እያመራ ይገኛል።



ምንም እንኳን ይህ ተከታታይ ወታደራዊ እርምጃ ጠላት የተባሉትን ኃይሎች ለማዳከም እና የኃይል ሚዛኑን ለማስጠበቅ የሚደረግ ስሌት እንደሆነ በየጎራው ባሉ መንግሥታት በኩል ቢገለጽም አሁን ባለው ተጨባጭ የዓለም ጂኦፖለቲካ ሁኔታ ግን እንዲህ ዓይነት የኃይል እርምጃ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና፣ የኤኮኖሚ ቀውስ እና ፍርሃትን ዳግም ፈጥሯል።

 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

27 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።