Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አስተያየት

የቲክቶከሮችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣት ጀርባ!

SM Samuel Mulgeta May 23, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 359 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የቲክቶከሮችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣት ጀርባ!

በጥቂት ጊዚያት ውስጥ አይሾው ስፒድ፤ ዴይላን ፔጅ፤ ባካሪ ሳኛ እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ኢትዮጵን ጎብኝተዋል፡፡

በቤተልሄም ሰለሞን!

 

ለረጅም ዓመታት በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ በአሉታዊና በአንድ ወገን ገፅታ ብቻ ስትሳል የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ ግን ታሪኳንና እውነታዋን በራሷ ልጆች፣ በአፍሪካውያንና በዓለም አቀፍ የዲጂታል ታሪክ ነጋሪዎች አማካኝነት በመቀየር ላይ ትገኛለች።

Advertisement
Your ad could be here — contact us



በተለይም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ዩቲዩበሮች፣ ቲክቶከሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ባለሙያዎች፣ የሀገራት መሪዎችና ቱሪስቶች ቀዳሚ የጉዞ መዳረሻ እየሆነች ትገኛለች።

 

በቅርቡ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን (ASMIS 2026) በደመቀ ሁኔታ ላስተናገደችው አዲስ አበባ ይህ እድል የኢትዮጵያን ቅርስ፣ ባህል እና የቱሪዝም ሀብት ለዓለም ገበያ ለማስተዋወቅ ታላቅ እድል ሆኖ ተገኝቷል።


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብነት እና ቀልብ ሳቢነት በተግባር ካሳዩት ታላላቅ ክስተቶች መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ጉልበቱና አስቂኝ ድርጊቶቹ የሚታወቀው አሜሪካዊው ወጣት ዩቲዩበሪ "አይሾው ስፒድ" በአዲስ አበባ ያደረገው ጉብኝት አንዱ ነበር።

 

IshowSpeed Arrives in Addis Ababa, Ethiopia



ይህም ቆይታ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ስለ ኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ታሪክ እንዲያውቁና ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እንዲፈልጉ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሮ አልፏል።




ይህንኑ የተጀመረውን ጉብኝት በመቀጠል በአሁኑ ወቅት 19 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉትና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታወቀው የይዘት አዘጋጅ ዲላን ፔጅ በአዲስ አበባ በመገኘት ሰፊ የባህልና የቅርስ ጉብኝት መርሃ ግብር ጀምሯል።




የእነዚህ ታዋቂ ግለሰቦች መጉረፍና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ቀልብ መሳብ የሀገሪቱን የቱሪዝም ገፅታ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው የሚገኝ ሲሆን በተለይም በቅርቡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት አዲስ በተገነቡት የአዲስ አበባ ሰፋፊ ጎዳናዎች፣ ዘመናዊ መብራቶችና ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች መካከል ሲጓዙ የሚያሳየው ቪዲዮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ "ቫይራል" መውጣቱ የዚህ ትልቅ ማሳያ ነው።



Image

 

የአርሰናል የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋች የሆነው ባካሪ ሳኛን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች በከተማዋ ሁለንተናዊ ለውጥና ውበት ላይ ያላቸውን ታላቅ አድናቆት መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ይዘት ፈጣሪዎቹ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ተከታዮቻቸው የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶች በማጋራት ሀገሪቱ ያላትን ጥንታዊ ማንነት ከዘመናዊነት ጋር እንዴት አዋህዳ እንደያዘች ያስተጋባሉ።



በአጠቃላይ የእነዚህ ግህለሰቦች ጉብኝት ዋነኛ ፋይዳው ኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መድባ ልታከናውነው የማይችለውን ሰፊ የቱሪዝም ማስተዋወቅ በማከናወን የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደጋቸው ነው።



ከዚህም ባሻገር ለዘመናት ስለ ሀገሪቱ የተገነቡትን የተዛባና አሉታዊ ትረካ በአንድ ጀንበር በመስበር አዲስ አበባ ምን ያህል ዘመናዊ፣ ውብና ሰላማዊ የቱሪስት መዳረሻ መሆኗን በተግባር ያሳያሉ።



ይህ ሂደት የሀገር በቀል ባህላዊ እሴቶችን፣ ምግቦችንና የቡና ሥነ-ሥርዓትን ለዓለም በማስተዋወቅ የባህል ቱሪዝምን ከማሳደጉም በላይ መዲናዋን ለአፍሪካ የዲጂታል ፈጠራ ዋነኛ ማዕከል በማድረግ አህጉራዊ ተፅዕኖዋን በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክረዋል።

 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

27 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።