Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ስፖርት

የሚካኤል አርቴታ አስገራሚ የቃለ-መጠይቅ ቆይታ!

SM Samuel Mulgeta May 21, 2026 Updated 1d ago 4 ደቂቃ ንባብ 456 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የሚካኤል አርቴታ አስገራሚ የቃለ-መጠይቅ ቆይታ!

የክለቡ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ሻምፒየን መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ የመጀመርያ ቃለ-መጠይቃቸውን ዛሬ ሰጥተዋል።

 በመኮንን አልማው

 

የሊጉ ሻምፒዮን መሆን ያላዘናጋቸው መድፈኞቹ በመጭው እሁድ ምሽት ከክሪስታል ፓላስ ጋር ላለባቸው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ልምምድ ሰርተዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


በተጨማሪም 9 ቀናት በኋላ ከፒኤስጂ ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ፍልሚያ የሚጠብቃቸው መድፈኞቹ በአመቱ ሁለተኛ ግዙፍ ዋንጫ ለማሳካት ጠንክረው እየሰሩ ነው።


የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን የሆኑት እና እሁድ ምሽት በክርስታል ፓላሱ ጨዋታ ዋንጫውን የሚረከቡት መድፈኞቹ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረታቸውን ሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው የልምምድ ጊዜም በሻምፒዮንስ ሊጉ ኳሶች ብቻ ሲሰሩ ታይተዋል።


የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ቢያሸንፉም ነገር ግን እስከአሁኗ ደቂቃ ድረስ በአንድም የእንግሊዝ ክለብ "እንኳን ደስ አላቹ" ያልተባሉት መድፈኞቹ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ትኩረታቸውን ሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ ያደረጉ ይመስላል።


ለቀጣዮ ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅታቸውን በጀመሩበት በዛሬው ክፍት የልምምድ ጊዜም አንዳንድ ቁልፍ ተጫዋቾች በቡድኑ ስብስብ ውስጥ አልታዩም።


ለረዥም ጊዜ በጉዳት ከሜዳ እርቆ የቆየው ሁለገቡ ተጫዋች ሚካኤል ሜሪኖ የዛሬውን ልምምድ ዘግየት ብሎ ተቀላቅሏል።


ተጫዋቾችም ከረጅም ግዜ በኋላ ለተመለሰው የቡድን አጋራቸው የእንኳን ተመለስክ አቀባበል አድርገውለታል።

 

Back to business: 60 pics as we return to training | Gallery | News |  Arsenal.com


ከሜዳ እርቆ የቆየው የመስመር ተከላካዩ ጁሪየን ቲምበር በበኩሉ አሁንም ከጉዳት ባለማገገሙ ምክንያት በዛሬው የጋራ የልምምድ መርሃ ግብር ላይ ሳይገኝ ቀርቷል።


ማክስ ዶውማንም እንዲሁ ከዛሬው የአርሰናል ልምምድ ውጪ ነበር። ምክንያቱም ወደ ትምህርት ቤት አምርቶ ፈተና መውሰድ ስለነበረበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡


በተጨማሪም የክለቡ ወሳኝ ተጫዋች የሆኑት ቡካዮ ሳካ ዊሊያም ሳሊባ እና ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ከስብስቡ ጋር አብረው ልምምድ እንዳልሰሩ ታውቋል።


ነገር ግን እነዚህ 3 ወሳኝ ተጫዋቾች ከስብስቡ ጋር ያልታዩት በጉዳት ምክንያት እንዳልሆነ ታውቋል።
ተጨዋቾቹ ከጉዳት ስጋት ነፃ እንዲሆኑ ስለተፈለገ እና የአካል ብቃት ማገገሚያ እንዲያደርጉ ተብሎ ለእያንዳንዳቸው በተዘጋጀ ልዩ የግል የልምምድ ቦታ ላይ ለየብቻቸው እንደሰሩ ተገልጿል።


የሻምፒዮኖቹ የቴክኒክ ክፍል ተጫዋቾቹን በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሲል በከፍተኛ ጥንቃቄ እየጠበቃቸው መሆኑ ተነግሯል።


የክለቡ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ሻምፒየን መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ የመጀመርያ ቃለ-መጠይቃቸውን ዛሬ  ሰጥተዋል።


የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መባል የማይታመን ስሜት ይፈጥራልሲሉ የተናገሩት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታእስካሁን በህይወቴ ምርጥ ስሜት ከፈጠሩልኝ መካከል አንዱ የሊጉ ሻምፒዮን የሚለው ድምጽ ነው" ብለዋል።


የማንችስተር ሲቲን ጨዋታ አለመመልከታቸውን የገለፁት አርቴታ እንዴት ልጃቸው እያለቀሰ እንዳበሰራቸው ሁነቱን ሲያስረዱከውስጥ ድምጽ ሰማሁ ልጄ በሩን በኃይል ከፍቶ ገብቶ ወደ እኔ እየሮጠ በእንባ በተሞላ ድምጽ 'አባዬ አባዬ ሻምፒዮን ሆንን ' ብሎ ነው ያበሰረኝይላሉ።


አርቴታ ቡድኑ ሻምፒየን መሆኑን ሰለሰሙበት አጋጣሚ ሲናገሩም "ከዛ ወዲያው ኦዴጋርድ በቪዲዮ ደወለለኝ አንስቼ ኦዴ... አልኩት እሱም አለቃ... አለኝ! እኛ እዚ እየተደሰትን ነው ቦስ የት ነህ አንተ ቶሎ አለኝ! እንዲ ያሉ አጋጣሚዎችን በቃላት መግለፅ በጣም ከባድ ነው! የሊጉ ሻምፒየን መባል ስሜቱ ልዩ ነው።" ሲሉ ነበር በፈገግታ የተናገሩት አርቴታ።


አክለውም "በለንደን ጎዳናዎች ላይ ከደጋፊዎቻችን ጋር ድሉን ስናከብር በአንድ ዋንጫ እንዲሆን አልፈልግም! ሁለት ዋንጫ ይዘን በክፍት ባስ መዞር ነው እቅዴ" በማለት ለሻምፒዮንስ ሊጉ ያላቸውን እቅድ አጋርተዋል።


የመድፈኞቹ አለቃ በዚህ የቃለመጠይቅ ቆይታቸው ስለቀድሞ ወዳጃቸው እና ተፎካካሪያቸው ጋርዲዮላ አንስተዋል።
"
ፔፕን ማመስገን ፈልጋለው ለብዙ ነገሬ መሰረቱ እሱ ነው። የመጀመሪያ የአሰልጣኝነት ህይወቴን የጀመርኩት ከሱ ጋር ነው! ሰለዚህ በእያንዳንዱ በደረስኩበት ምዕራፍ ሁሌ እሱን ማመስገን ፈልጋለሁ" ብለዋል።


ካለፉት አመታት ምን እንደተማሩ የተጠየቁት ሚኬል አርቴታትሁት መሆን እና ለማወቅ መጓጓትንሲሉ መልሰዋል።


አክለውም "ብዙ ማሸነፍ ተምሪያለው ደጋግመን ሞክረን በመጨረሻም አሸንፈናል ይሄን የተማርኩት በትዕግሥት እና በትህትና ነው።" የሚሉት ስፓኒያርዱ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ
"
ከዚህ በኋላም እንዲሁ ትሁት ሆኜ እቀጥላለሁ ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን መማር እና መሞከር ፈልጋለው" ሲሉ ተደምጠዋል።


ያለፉት 48 ሰዓታት ለእሳቸውጅግ የተለዩ እና አስደሳች እንደነበሩ በመግለጽ "በህይወቴ ተስምቶኝ የማላቀው ልዩ ስሜት ነው ማክሰኞ የተሰማኝ።" ያሉት ሚኬል አርቴታ በእነዚያ ጊዚያትም ከልጅነት ወዳጃቸው እና ከአሁኑ የበርንማውዙ አሰልጣኝ ኢራኦላ ጋር ማውራታቸውን አልደበቁም።


"
ትናንት ኢራኦላ ጋር ተደዋውለን ነበር።" ያሉት አርቴታ "የሊጉ ሻምፒዮን ሰለሆንክ እንኳን ደስ አለህ አለኝ እኔም በበርንማውዝ ቤት ሰለነበረው አስደናቂ ብቃት አሞገስኩት" ብለዋል።


አክለውም "ኢምሬትስ ላይ እኛን አሸንፋችሁ ዋንጫውን ልታስነጥቁን ነበር ግን መልሳችሁ ስለሰጣችሁን አናመሰግናለን አልኩት! በአጠቃላይ ሁለታችንም ከተመሰጋገንን በኋላ ስልኩ ተዘግቷል።" ሲሉ የነበራቸውን የስልክ ልውውጥ ቋጭተዋል።


በመጨረሻም አርቴታ የምስጋና መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ "በዙሪያዬ የነበራችሁ በሙሉ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ! ይህ ድል በእኔ ብቻ የተመዘገበ አይደለም! ከእኔ ጀርባ ብዙ ብዙ ሰዎች አሉ። ለሁላቹም እዚህ ላላችሁትም ሆነ በመላው አለም ለምትገኙት ደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን መልካም የደስታ ጊዜ።" በማለት የቃለ-መጠይቅ ቆይታቸውን ቋጭተዋል።

 

 

SM
ስለ ጸሐፊው

Samuel Mulgeta

27 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።