Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ኤምሬትስ በኢራን ላይ ሚስጥራዊ ወታደራዊ ጥቃቶችን መፈጸሟ ተገለጸ

A Administrator May 15, 2026 Updated 4h ago 2 ደቂቃ ንባብ 76 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኤምሬትስ በኢራን ላይ ሚስጥራዊ ወታደራዊ ጥቃቶችን መፈጸሟ ተገለጸ

ግንቦት 4/2018 (ገበያ ሚዲያ) የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጎን በመሰለፍ በኢራን ላይ በሚሰነዘሩ ወታደራዊ ጥቃቶች ውስጥ በምስጢር እየተሳተፈች መሆኑን የወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። ዎል ስትሪት ጆርናል ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኤምሬትስ ጦር ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በሚገኘው የኢራን የላቫን ደሴት የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል።ይህ በኤምሬትስ በኩል በይፋ ያልታመነው ጥቃት በማጣሪያው ላይ ከፍተኛ እሳት ያስከተለ ሲሆን ተቋሙንም ለወራት ከአገልግሎት ውጭ አድርጎታል። ይህ እርምጃ አቡ ዳቢ በቀጣናው እየተካሄደ ባለው የኢራን ጦርነት ውስጥ ያላትን ሚና ከመከላከል ወደ ቀጥተኛ ጥቃት አድራጊነት መለወጧን የሚያሳይ እንደሆነ ተነግሯል።ኢራን ጥቃቱን “የጠላት ወረራ” ስትል የጠራችው ሲሆን በኤምሬትስ እና በኩዌት ላይ ከ2,800 በላይ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን በማስወንጨፍ የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች። ይህ ከእስራኤል በበለጠ በኤምሬትስ ላይ ያተኮረው ጥቃት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሏል።በዚህም በዱባይ እና በአቡ ዳቢ የአክሲዮን ገበያዎች ላይ ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ሀብት የወደመ ሲሆን ከ18,400 በላይ በረራዎች በመሰረዛቸው የአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ክፉኛ ጎድቶታል።በተጨማሪም በሪል ስቴት እና በሌሎች ቁልፍ የንግድ ዘርፎች ላይ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸውን በብዛት እያሰናበቱ ይገኛሉ።የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ያላት ወታደራዊ ቅንጅት መጠናከሩ ጦርነቱን ይበልጥ እያባባሰው እንደሆነ ተንታኞች የሚገልጹ ሲሆን ዋሽንግተን የአቡ ዳቢን ወታደራዊ ተሳትፎ በምስጢር መደገፏ ኤምሬትስ ከአሜሪካና ከእስራኤል ስትራቴጂያዊ ዓላማ ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣሟን የሚያረጋግጥ ሆኗል።በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ በኢራን ሰማይ ላይ የታዩ ማንነታቸው ያልታወቁ ተዋጊ ጄቶች እና በሺራዝ አካባቢ የተከሰከሰችው የቻይና ምርት የሆነችው ‘ዊንግ ሉንግ 2’ ድሮን ኤምሬትስ በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረገች ስለመሆኑ የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች እንደነበሩ ይታወሳል። ኢራን ለሳውዲ ዓረቢያ እና ለኦማን በሰጠችው ማስጠንቀቂያ ኤምሬትስ ለምትፈጽመው ጥቃት የአጸፋ እርምጃው በከፍተኛ ሁኔታ አቡ ዳቢ ላይ እንደሚያተኩር በመግለጽ አገሪቱን ከጎረቤቶቿ ለመነጠል እየሞከረች እንደሆነም ተገልጿል።በሌላ በኩል በኤምሬትስ እና በሳውዲ ዓረቢያ መካከል ያለው የቆየ ውጥረት እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ኤምሬትስ በቅርቡ ከኦፔክ አባልነት መውጣቷና በኢራን ጦርነት ዙሪያ የያዘችው የተለየ አቋም በባሕረ ሰላጤው አገራት መካከል ያለውን ልዩነት ይበልጥ እያሰፋው መሆኑ ተመላክቷል።

 

A
ስለ ጸሐፊው

Administrator

12 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።