Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አለም አቀፍ ትንታኔ

በሩሲያ ጦርነት እየተሳተፉ ነው የተባሉ 34 ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር ወጣ

BS Bethelhem Solomon Jul 8, 2026 Updated 10h ago 2 ደቂቃ ንባብ 720 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በሩሲያ ጦርነት እየተሳተፉ ነው የተባሉ 34 ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር ወጣ

ለሩሲያ ጦር ተሰልፈው የሚዋጉ ኢትዮጵያውያንን ስም ይፋ ያደረገው ፕሮጀክቱ ከእነዚህ መካከል ቢያንስ 3ቱ መሞታቸውን አስታውቋል።


በዩክሬን
መንግስት የስለላ ተቋም ስር የሚንቀሳቀሰው  “I Want to Live” የተሰኘው ፕሮጀክት በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ያላቸውን 34 ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።



ለሩሲያ ጦር ተሰልፈው የሚዋጉ ኢትዮጵያውያንን ስም ይፋ ያደረገው ፕሮጀክቱ  ከእነዚህ መካከል ቢያንስ 3 መሞታቸውን አስታውቋል።



ፕሮጀክቱ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለሩሲያ ጦር ኃይል የፈረሙት በተለያየ ጊዜ ሲሆን .. ዲሴምበር 24 ቀን 2024 . 8ቱ፣ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2025 ደግሞ 10ሩ፣ እንዲሁም ኦክቶበር 30 ቀን 2025 በተመሳሳይ 9 ሰዎች ኮንትራት መፈጸማቸውን አስፍሯል።



እነዚህ ኢትዮጵያውያን ኮንትራቱን የፈረሙት በቀጥታ ከሩሲያ ጦር ኃይል ጋር ሳይሆን፤ በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሆነ ተገልጿል።


ይፋ ከሆኑት 34 ግለሰቦች መካከል በእድሜ ትንሹ የሆኑት አዱኛ አሮንና ዘለቀ ናትናኤል መሆናቸውን ገልጾ፤ እድሜያቸው 20ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሷል።



በእድሜ ትልቁ ደግሞ ሀብተማሪያም ስንታየሁ የተባሉ ግለሰብ መሆናቸውንና እድሜያቸውም 50 ዓመት መሆኑን በማስቀመጥ አነጻጽሯል።


ፕሮጀክቱ እንዳለው የእነዚህን 34 ኢትዮጵያውያን ስም ለማወቅ የቻለ ቢሆንም በሩሲያ ጦር ኃይል ውስጥ ተሰልፈው እየተዋጉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ግን በርካታ ናቸው ተብሏል



አክሎም እስካሁን ባለው መረጃ 40 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 2,984 ሰዎች ለሩሲያ እየተዋጉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 6 ሕይወታቸው ማለፉን ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል።



በሌላ
በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (/) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በትናንትናው እለት አነጋግረዋል፡፡


ከሁለት አመት በፊት በሩሲያ እና በዩክሬይን መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ ዓለም አቀፍ ትኩረት በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ላይ አርፎ እንደነበር ይታወሳል።



በዚህም
በመቶዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሩሲያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ተሰልፈው ለመዋጋት ያላቸውን ፍላጎት ለመግለጽና ዝርዝር መረጃቸውን ለማስገባት በኤምባሲው ደጃፍ ረጅም ሰልፍ ፈጥረው ነበር።

Advertisement
Your ad could be here — contact us


በስፍራው
የተገኙት አመልካቾች በወቅቱ በሩሲያ በኩል ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነ እንደሰሙ ገልጸው የነበረ ሲሆን የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ  እነዚህ ሰዎች የተሰለፉት ለውትድርና ምልመላ ሳይሆን ለሩሲያ ፌዴሬሽን ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ መሆኑን አስታውቆ ነበር።


የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ይፋዊ መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን፤ ኤምባሲው መግለጫውን ከሰጠ በኋላ በስፍራው የነበረው ውጥረት ቀዝቀዝ ብሎ ነበር።


ይሁን እንጂ ክስተት በወቅቱ በኢትዮጵያዊያን የቀድሞ ወታደሮች ዘንድ የነበረውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተፅዕኖና የስራ አጥነት ችግር በማሳየቱ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።