Home / ገበያ ቢዝነዝ / ስኳር ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ሆኖ እንዲቀጥል ተወሰነ

ስኳር ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ሆኖ እንዲቀጥል ተወሰነ

የካቲት 26/2018 (ገበያ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር ባገኘው ማብራሪያ መሠረት፤ ስኳር ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለሚፈጸምባቸው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በሙሉ ባስተላለፈው መመሪያ፤ ቀደም ሲል የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1287/2015 ከፀደቀ በኋላ ስኳር ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ የጸና መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ቀደም ሲል በሐምሌ 28/2017 የወጣው መመሪያ የጉምሩክ ታሪፍን ብቻ የሚመለከት እንጂ፤ በኤክሳይዝ ታክስ ነፃ መሆን ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ተብራርቷል።

በሌላ በኩል እስከዛሬ የታክስ እፎይታ ሲደረግለት የነበረው የአብሽ ምርት፤ አሁን ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዲከፈልበት መወሰኑ በመመሪያው ተመላክቷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለኮሚሽኑ በላከው ማብራሪያ አብሽ በባህሪው ከእህልና ከጥራጥሬ ወገን ስለማይመደብ በታክስ ነፃ ዝርዝር ውስጥ ሊካተት እንደማይችል ገልጿል።

ይህ አዲስ የሥራ መመሪያ በሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፎች በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ እንዲደረግ የታዘዘ ሲሆን፤ በንግድ ማህበረሰቡ እና በሸቀጦች ዋጋ ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ገበያ_ሚዲያ#gebeyamedia#gebeyanews#ገበያ#Ethiopia#ኢትዮጵያ#addisababa#አዲስአበባ#Customs#Tax#sugar#Vat#Excisetaxes#የጉምሩክኮሚሽን#ታክስ#ስኳር#አብሽ#ኢኮኖሚ#አዲስመመሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *