Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

በ75 የመንግስት ተቋማት ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ 187 ሚሊዮን ብር ግድፈት ተገኘ

BS Bethelhem Solomon Jun 16, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 36 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በ75 የመንግስት ተቋማት ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ 187 ሚሊዮን ብር ግድፈት ተገኘ

በእነዚህ የፋይናንስ ግድፈቶች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱንም ቢሮው አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ባከናወነው አጠቃላይ የኦዲት ምርመራ 75 የመንግስት ተቋማት ውስጥ የተፈጸሙ የፋይናንስ ጉድፈቶች ማግኘቱን አስታወቋል።


በቢሮው የተለየው 187.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የፋይናንስ ግድፈት ላይ ወዲያውኑ የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን የቢሮው ሃላፊዎች ገልጸዋል።

ይህ የኦዲት ውጤት ይፋ የሆነው ከተማ አስተዳደሩ 350 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ከፍተኛ የመሠረተ ልማት እና የህዝብ አገልግሎት የፋይናንስ ክፍተት ባጋጠመው ወቅት ነው።

ቢሮው ያለውን ውስን የፋይናንስ አቅም በብቃት ለመምራት እና የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት የፋይናንስ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ባለፈው ዓመት የነበረውን የኦዲት እቅድ አፈጻጸም 171 በመቶ በማሳደግ የቁጥጥር ስራውን ወደ 3,242 ተቋማት ማስፋት ችሏል።


የኦዲት ሪፖርቶች ጥራትም ወደ 85 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉ የቢሮውን የክትትል አቅም ማደግ የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን ይህ የላቀ አፈጻጸም የአዲስ አበባን የፋይናንስ አስተዳደር ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ያስቻለ ነው ተብሏል።


በአፍሪካ ከተሞች መካከል በተደረገ የፋይናንስ አስተዳደር ግምገማ አዲስ አበባ ከአህጉሪቱ ታላላቅ ከተሞች መካከል ቀዳሚ ሆና መመረጧን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።


በጥር 14 ቀን 2018 . በተካሄደ የክልላዊ የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት ላይ ይፋ እንደተደረገው አዲስ አበባ በገቢ አሰባሰብ እና በፋይናንስ ሀብት ምደባን ጨምሮ በስድስት ዋና ዋና መመዘኛዎች ውስጥ በአምስቱ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከናይሮቢ፣ ዳሬሰላም፣ ሉሳካ፣ ኪጋሊ እና ያውንዳ መሪ መሆን ችላለች።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

የፋይናንስ ቁጥጥር ስራውን ዘመናዊ እና ውጤታማ ለማድረግ ቢሮው በሰው ኃይል እና በአሰራር ሂደት ላይ ትኩረት ማድረጉን አስታውቋል።


በአሁኑ ወቅት የውስጥ ኦዲት ስራውን የሚመሩት 80 በመቶ የሚሆኑት ባለሙያዎች ረጅም የሥራ ልምድ ያላቸው መሆናቸው ቢሮው ተግዳሮቶችን አስቀድሞ በመለየት ለመፍታት ለሚከተለው ስልት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጿል።

የቢሮው ሃላፊዎች እንደገለጹት የተጠናከረ የፋይናንስ ቁጥጥርና የኦዲት አፈጻጸም ለልማት አጋሮች እና ለውጭ አበዳሪ ተቋማት ያለውን እምነት ለማስቀጠል ወሳኝ ነው።


ይህም ከተማዋ በመሠረተ ልማት ግንባታ እና በህዝብ አገልግሎት መስጫ ዘርፎች የገጠማትን 350 ቢሊዮን ብር የፋይናንስ ክፍተት ለመሙላት በሚደረገው ጥረት የገንዘብ ምንጮችን ለመሳብ እና በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ መተማመንን ለመገንባት የሚያግዝ ስትራቴጂክ እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህ የሪፎርም ጉዞ አዲስ አበባ የፋይናንስ ግልጽነትን በማረጋገጥ የከተማ ልማት ዘላቂነትን ለመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየወሰደች ያለችውን የለውጥ እርምጃ ያሳያል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

7 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።