Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነዝ

የ2019 የፌዴራል በጀት በብር ከፍተኛ ዕድገት ቢያሳይም በዶላር ሲሰላ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኘ

BS Bethelhem Solomon Jun 15, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 11 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የ2019 የፌዴራል በጀት በብር ከፍተኛ ዕድገት ቢያሳይም በዶላር ሲሰላ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኘ

በ2013 ዓ.ም 13.6 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የበጀት መጠን፤ በ2019 ዓ.ም 14.9 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ሁኗል

በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት በጀት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብር ሲሰላ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ቢታወቅም በተመሳሳይ ጊዜ በዶላር ሲሰላ የታየው ለውጥ ግን ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱ ተመላክቷል።


2013 . በኋላ በኢትዮጵያ የነበረው የበጀት ዕድገት በብር ሲሰላ እስከ 480 በመቶ የደረሰ ቢሆንም ይህ በጀት በዶላር በመለወጥ ሲሰላ የዕድገቱ መጠን 8 በመቶ ጭማሪ ብቻ በማሳየት ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል።


በሁለቱ መገበያያ ገንዘቦች መካከል ያለው የዕድገት ልዩነት በግልጽ እንደሚንፀባረቀው ከሆነ የፌዴራል በጀት 2013 . 476 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን 2019 . ወደ 2.3 ትሪሊዮን ብር ከፍ ብሏል።


2013 . ጀምሮ የተመዘገበውን የበጀት ዕድገት ስንመለከት 2013 . 476 ቢሊዮን ብር፣ 2014 . 561 ቢሊዮን ብር፣ 2015 . 786 ቢሊዮን ብር፣ 2016 . 801 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም 2017 . ወደ 971 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።


ይህ የበጀት ዕድገት 2018 . ወደ 1.9 ትሪሊዮን ብር የተጠጋ ሲሆን 2019 . ደግሞ ወደ 2.3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።


በሌላ በኩል በዶላር ሲሰላ 2013 . 13.6 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የበጀት መጠን፤ 2019 . 14.9 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ሁኗል


የፌዴራል
መንግሥት 2019 በጀት ዓመት ያዘጋጀው 2.339 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰሞኑ ቀርቦ የነበረ ሲሆን አዲሱ በጀት ከ2018 1.9 ትሪሊዮን ብር በጀት አኳያ ዕድገት ቢያሳይም በዶላር ሲሰላ ተቀራራቢ ሆኖ ተገኝቷል።


የበጀት ረቂቁን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ በጀቱ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ግቦች ለማሳካትና የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊፈጥር የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።


2019 በጀት ዓመት ከቀረበው ጠቅላላ በጀት ውስጥ 1.236 ትሪሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 568.2 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 520.6 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግብ ማስፈጸሚያ የተመደበ መሆኑ ተገልጿል።


በበጀት ዓመቱ የፌዴራል መንግሥት ጠቅላላ ገቢ 1.817 ትሪሊዮን ብር እንዲሆን ግምት የተወሰደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1.6 ትሪሊዮን ብር ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ ታቅዷል።


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው የቀረበው ረቂቅ በጀት የመንግሥትን የልማት ዕቅዶች ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርተውታል።


ይሁን እንጂ በብር እና በዶላር የተያዘው የበጀት መጠን መካከል ያለው ይህ ሰፊ የዕድገት ክፍተት በኢኮኖሚው ውስጥ እየታየ ያለውን የዋጋ ግሽበትና የብር መግዛት አቅም መዳከም ነጸብራቅ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

4 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።