በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የንግድ ውድድር ተከትሎ ምርትን ማስተዋወቅ እና ማስታወቂያ ስራዎች በገበያው ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቦታ እየያዙ መጥተዋል።በተለይም በአሁኑ ወቅት የንግድ ማህበረሰቡ ምርትና አገልግሎቱን ለሸማቹ ለማድረስ በርካታ አማራጮችን እየተጠቀመ ይገኛል።
በመንግሥት ባለቤትነት ስር የሚገኙ የጅምላ መገናኛ ብዙኃን ማለትም ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ጋዜጦች አሁንም ድረስ ሰፊ ተደራሽነት ያላቸው ሲሆን፤ በተጓዳኝም በግል ባለሀብቶች የተያዙ መጽሔቶች፣ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች፣ የሬዲዮ ጣቢያዎች እና በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች (ቢልቦርዶች) ዋነኞቹ የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገዶች ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ሪፖርተር (The Reporter)፣ አዲስ ፎርቹን (Addis Fortune)፣ ካፒታል (Capital)፣ ፕሬስ ዳይጀስት (Press Digest)፣ ዘ ዴይሊ ሞኒተር (The Daily Monitor)፣ አዲስ ዜና፣ አዲስ ዘመን፣ ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ (The Ethiopian Herald)፣ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርቶች፣ እንዲሁም በውጭ ሀገራት የሚገኙት እንደ ኢትዮጵያን ሪቪው (Ethiopian Review)፣ ኢሳት (ESAT)፣ ኢትዮሚዲያ (Ethiomedia) እና ዋልታ ፎረም (Walta Forum) ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የአማርኛ የዜና ስርጭት ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ቻናሎች ማለትም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ አዲስ ዋልታ፣ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ)፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ኢቢኤስ፣ አርትስ፣ ዓባይ፣ገበያ ሚዲያ እና ሀገሬ ያሉ ገጾች በማስታወቂያው ዘርፍ ፋና ወጊ ናቸው።

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ከሚሰሩ መደበኛ የማስታወቂያ ስራዎች በተጨማሪ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር የንግድ ትርኢቶች (ትሬድ ፌር) እና ባዛሮች እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
እነዚህ የንግድ ትርኢቶች በተለይም ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከአውሮፓ እንዲሁም በርካታ የሀገር ውስጥ አምራቾችን እና ላኪዎችን በአንድ መድረክ በማገናኘት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።
እንዲህ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረኮች መዘጋጀታቸው የሀገር ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ከአለም አቀፍ አቻዎቹ ጋር በቀጥታ በመገናኘት የንግድ ልምድ እንዲለዋወጥ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን እንዲመለከት እና አዳዲስ የገበያ አማራጮችን በስፋት እንዲቃኝ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑ ይገለጻል።
በተለይም እነዚህን የባዛር እና የማስታወቂያ ዕድሎች ጀማሪ ነጋዴዎች እና ስራ ፈጣሪዎች ሲሳተፉ በአጭር ጊዜ የሚገኝ የሽያጭ ትርፍ ላይ ባለማተኮር የረጅም ጊዜ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ የሚፈጥሩበትን እድል ይከፍታሉ ።
ወደ አውደ-ርዕዩ የሚመጡ ጎብኚዎችን አድራሻ እና ፍላጎት በጥንቃቄ በመመዝገብ ከባዛር በኋላም ቀጣይነት ያለው የደንበኝነት ግንኙነት መገንባት እና የዲጂታል ማስታወቂያ አማራጮችን በመጠቀም የባዛር ተሳትፎን አስቀድሞ ለታለመው ደንበኛ ማሳወቅ መቻል ተወዳዳሪ የንግድ ሰው ለመሆን እንደሚረዱ ይመከራል።