Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ተጨማሪ ወታደር ማሰማራቷ ተገለጸ

A Administrator May 14, 2026 Updated 3h ago 1 ደቂቃ ንባብ 51 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ተጨማሪ ወታደር ማሰማራቷ ተገለጸ

ሚያዚያ 30/2018 (ገበያ ሚዲያ) የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የብሉ ናይል እና አወዛጋቢ በሆነው የአል-ፋሻጋ አካባቢዎች ተጨማሪ ወታደሮችን እና የጸረ-አውሮፕላን መከላከያ መሣሪያዎችን ማሰማራቱ ተዘገበ።

ይህ የኃይል ማጠናከሪያ እርምጃ የተወሰደው ሱዳን “ኢትዮጵያ ለድሮን ጥቃት መነሻ ሆናለች” የሚል ክስ ካቀረበች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።

የሱዳን ጦር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ በሆነው የብሉ ናይል ግዛት አዳዲስ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ብሉምበርግ ዘግቧል ።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

የሱዳን ጦር የሥራ ኃላፊዎች አካባቢውን ከጎበኙ በኋላ የጸጥታ ጥበቃው እንዲጠናከር ትዕዛዝ መስጠታቸውም ተመላክቷል።

በተጨማሪም የሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው ከሆነ በገዳሪፍ ግዛት በሚገኙት ምስራቅ ገላባት፣ ባሱንዳ እንዲሁም በታላቁ እና በታናሹ አል-ፋሻጋ አካባቢዎች የሱዳን ጦር ተጨማሪ የጦር መሣሪያዎችንና ወታደሮችን በስትራቴጂካዊ ስፍራዎች ላይ አኑሯል።

ይህ ወታደራዊ ዝግጅት የመጣው ሱዳን “በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ለተሰነዘረው የድሮን ጥቃት ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እጃቸው አለበት” ስትል ከወነጀለች በኋላ ነው።

ኢትዮጵያ በበኩሏ የቀረበባትን ክስ “መሰረተ ቢስ” ስትል ውድቅ ያደረገች ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ክሱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥንና የሰላም ጥረቱን የሚያደናቅፍ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም አንዳንድ የሱዳን የጦር ወገኖች የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እየጣሱ መሆኑን ሚኒስቴሩ መልሶ ከስሷል።

አወዛጋቢው የአል-ፋሻጋ የድንበር አካባቢ ለረጅም ጊዜ በሁለቱ አገራት መካከል የውጥረት ምንጭ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን የተጀመረው አዲስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቀጠናውን ሰላም ይበልጥ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ተሰግቷል።

A
ስለ ጸሐፊው

Administrator

12 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።