Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ትምህርታቸውን ያቋረጡ የመጀመሪ ደረጃ ተማሪዎች በአመት ሁለት ክፍል እንዲያልፉ የሚፈቅድ መመሪያ ጸደቀ

BS Bethelhem Solomon Nov 10, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 296 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ትምህርታቸውን ያቋረጡ የመጀመሪ ደረጃ ተማሪዎች በአመት ሁለት ክፍል እንዲያልፉ የሚፈቅድ መመሪያ ጸደቀ

በተመሳሳይ በመደበኛው 2ኛ ክፍልን አጠናቀው ለሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ለደረጃ ሁለት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት በአንድ ዓመት ተምረው በማጠናቀቅ በቀጣይ በመደበኛ ትምህርት 5ኛ ክፍል ገብተው መማር ይችላሉ እንደሚችሉ ተካትቷል።



በተለያዩ
ምክንያቶች ሁለትና ከዛ በላይ አመታት በትምህርት ገበታቸው ላይ ላልተገኙ እና መደበኛ ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ የመጀመሪ ደረጃ ተማሪዎች በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የውጭ ስደተኛ ጣቢያ የሚሰጥ በአንድ አመት ሁለት ክፍል እንዲያልፉ የሚፈቅድ መመሪያ ጸድቋል።



መመሪያው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች በመደበኛው የትምህርት ፕሮግራም ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ እና እድሜያቸው ከ12 እስከ 14 ዓመት ለሆናቸው ልጆች በማካካሻ በአንድ አመት ሁለት ክፍል እንዲያልፉ ይፈቅዳል።



በጥቅምት ወር “መደበኛ ያልሆነ የተፋጠነ ትምህርት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1160/2019” በሚል በትምህርት ሚኒስቴር በጸደቀው መመሪያ በአንድ አመት ሁለት የትምህርት ደረጃን እንዲሻገሩ የተፈቀደው ከአንድ እስከ ሦስተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ነው።



የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የውጭ አገር ስደተኛ ልጆችን ተጠቃሚ የሚያደርገው መመርያው የራሱ የሆነ የትምህርት ካላንደር የሚዘጋጅለት ሲሆን የመማር ማስተማሩ ተግባር የሚከናወነው ከህፃናት ከእለት ተእለት ኑሮ ጋር ተስማሚ በሆነ ጊዜ እንደሆነ ጠቅሷል።



ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሰጠው የተጨመቀው ስርዐተ ትምህርቱ ሁለት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን በደረጃ አንድ ማለትም የመደበኛ 1ኛ እና 2ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርት ተጨምቆ ለአንድ ዓመት ተዘጋጅቷል። ደረጃ ሁለትም እንዲሁ የመደበኛ 3ኛ እና 4ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርት ተጨምቆ ለአንድ ዓመት የተዘጋጀ ነው።

 
በዚህም መሰረት የደረጃ አንድ ትምህርትን ያጠናቀቀ ተማሪ በመደበኛው ወደ 3ኛ ክፍል የሚገባ ሲሆን የደረጃ ሁለትን ያጠነቀቀ ደግሞ በመደበኛው ወደ 5ኛ ክፍል የሚዛወር ይሆናል።


በተመሳሳይ በመደበኛው 2ኛ ክፍልን አጠናቀው ለሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ለደረጃ ሁለት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት በአንድ ዓመት ተምረው በማጠናቀቅ በቀጣይ በመደበኛ ትምህርት 5ኛ ክፍል ገብተው መማር ይችላሉ እንደሚችሉ አካቷል።


ለተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም የራሱ የሆነ የተማሪው የመማሪያ መጽሐፍት፣ የመምህር መምሪያ፣ እና አጥጋቢ የብቃት መለኪያ ይኖረዋል የሚለው መመሪያው በተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም የሚሳተፉ ልጆች ወደ ፕሮግራሙ ሲመጡ ያሉበትን ደረጃ ለመለየትና ለመመደብ የሚያስችል ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት ምዘና እንደሚወስዱ አብራርቷል፡፡


የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራምን እንዲተገብሩ የሚመረጡ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በዙሪያቸው ብዙ ከትምህርት ገበታ ውጭ ወይም መሠረታዊ ክህሎቶችን ሳይጨብጡ ያቋረጡ ህፃናት ያለባቸው መሆኑ በጥናት የተለዩ መሆን አለባቸው።


ፕሮግራሙ እንደ አስፈላጊነቱ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ወይም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ በሚያስተባብረው የሳተላይት ማዕከል እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ በመረጠው ቦታ በሚቋቋም ማዕከል ውስጥም የሚሰጥ ይሆናል ።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

94 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።