Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

አሜሪካ በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ የኩባንያዎቿ ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥረት እያደረገች ነው ተባለ ተባለ

BS Bethelhem Solomon Aug 1, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 95 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
አሜሪካ በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ የኩባንያዎቿ ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥረት እያደረገች ነው ተባለ  ተባለ

አየር መንገዱ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ በራሱ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን ክፍያ የአፍሪካ ልማት ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመሸፈን ቃል መግባቱን ጨምሮ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ይሸፈናል።


አሜሪካ
በኢትዮጵያ እየተገነባ ባለው 12.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች ጠንካራ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑን አስታወቀች።


ሐምሌ 22 ቀን 2018 .. በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሎጂስቲክስ እና ግንኙነት ሲምፖዚየም ላይ የተሳተፉት የአሜሪካ የንግድ ዲፓርትመንት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት ጋር በተደረጉ ውይይቶች ፕሮጀክቱ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ምክትል ረዳት ሚኒስትሩ አውሮፕላን ማረፊያው ለአየር መንገዱ ዕድገት የሚኖረውን ትልቅ ፋይዳ አድንቀው፤ ፕሮጀክቱ አፍሪካን ከቀጣናው እና ከዓለም ጋር ለማገናኘት በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ የቦይንግ አውሮፕላኖች በጂኢ ኤሮስፔስ  ሞተሮች ታግዘው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።


የአሜሪካ መንግሥት በተለያዩ መዋቅሮቹ አማካይነት ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረቶች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው፤ የንግድ ዲፓርትመንትም የአሜሪካን ኩባንያዎች ተሳትፎ ለማረጋገጥ በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለኢንጂነሪንግ፣ ግዥ፣ ግንባታ እና ፋይናንስ ውሎች የተዘጋጁትን አራት ዋና ዋና የሥራ ፓኬጆች የቅድመ-ብቃት ማጣሪያ ያጠናቀቀ ሲሆን ከቻይና፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ቱርክ፣ ህንድ እና ራሺያ የተውጣጡ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች እና ጥምረቶች ወደ ቀጣዩ የጨረታ ምዕራፍ አልፈዋል።


እነዚህ ፓኬጆች ዋናውን ተርሚናል፣ የድጋፍ መስጫ ተቋማት፣ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን እና ከግንባታው ውጭ ያሉ የመጓጓዣ ትስስሮችን ያካትታሉ።የቦታ ማስተካከያ እና መሰረታዊ የምድር ሥራዎች ጥር 2018 የተጀመሩ ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ 610 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የምድር ሥራ ይከናወናል ተብሏል


አየር መንገዱ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ በራሱ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን ክፍያ የአፍሪካ ልማት ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመሸፈን ቃል መግባቱን ጨምሮ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ይሸፈናል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ስድስት ቦይንግ 787-9 ድሪምለይነር አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ጋር የነበሩትን አማራጮች ወደ ጽኑ የትዕዛዝ ስምምነት መለወጡ ይታወሳል።


አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ትልቁን የቦይንግ 787 መርከብ የሚቆጣጠር ሲሆን፤10 ቦይንግ 787-9ዎችን እና 20 ቦይንግ 787-8ዎችን ይዞ እየሰራ ይገኛል። በተጨማሪም ጥር ወር ላይ ዘጠኝ ተጨማሪ ቦይንግ 787-9ዎችን ለማዘዝ ማስታወቁ ይታወሳል።

ማርክ ሚቸል አያይዘውም አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያዎች ምቹ የንግድ ከባቢ ለመፍጠር እንደምትሰራ ገልጸው የኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳዎች ለአሜሪካ ኩባንያዎች እውነተኛ የንግድ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

57 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።