Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ኤርትራ በኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና በጂኦፖለቲካዊ ትንታኔዎች ላይ መግለጫ አወጣች

BS Bethelhem Solomon Jul 25, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 314 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኤርትራ በኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና በጂኦፖለቲካዊ ትንታኔዎች ላይ መግለጫ አወጣች

የኢትዮጵያ መንግሥት ብሔራዊ ጥቅም ከማንኛውም ድርድር በላይ የሚቆም «ቀይ መስመር» መሆኑን አበክሮ መግለጹ ይታወሳል።


የኤርትራ
መንግሥት ኢትዮጵያ በባህር በር ባለቤትነት ዙሪያ የምታነሳቸውን ጥያቄዎች እና ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚነሱ የጂኦፖለቲካ ትንታኔዎችን በተመለከተ ጠንካራ እና አጠቃላይ አቋም ማንጸባረቁን የጣሊያኑ ቨሪታ ጋዜጣ ዘግቧል።

በሮማ የኤርትራ አምባሳደር ሰሃጽዮን ጴጥሮስ መንግስቱ ለታዋቂው የጣሊያን ጋዜጣ በላኩት ሰፊ የማስተካከያ ጽሑፍ፤ ኤርትራ በየትኛውም ወገን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ስር የምትወድቅ ሀገር እንዳልሆነች እና የሉዓላዊነት ጥያቄዎችን በምንም መልኩ እንደማትቀበል አጽንኦት ሰጥተዋል

አምባሳደሩ በደብዳቤያቸው መግቢያ ላይ እንደ ሆርን ሪቪው  ያሉ መገናኛ ብዙኃን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተጣጣሙ በመሆናቸው ገለልተኛ እና ሐቀኛ ምንጮች ሊባሉ እንደማይችሉ አስፍረዋል

እነዚህ አካላት የኢትዮጵያን መንግሥት ፖሊሲዎች እናሉዓላዊየተባለ የባህር በር ፍላጎት ያለማቋረጥ እንደሚደግፉ ጠቁመው ጉዳዩ በሐሰተኛ ትርክቶች ብቻ እየተቃኘ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

በተጨማሪም ኤርትራ ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ ለንግድ እንዳትጠቀም አድርጋለች የሚለው ውንጀላ ፍጹም ሐሰት መሆኑን አምባሳደሩ አብራርተዋል።


የኤርትራ ወደቦች ለንግድ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉት በሁለቱ አገራት መካከል በሚደረጉ ነፃ የንግድ ስምምነቶች እና በጋራ የኢኮኖሚ ጥቅም ላይ ተመስርተው ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።


ሆኖም
ከንግድ ትብብር ባሻገር የባህር በር አጠቃቀምን ከማንኛውም የሉዓላዊነት ጥያቄ፣ የግዛት መቆጣጠር ፍላጎት ጋር ማያያዝ ፍጹም እንደማይቻል አጽንኦት ሰጥተዋል።


ኢትዮጵያ
የንግድ አገልግሎቶችን እና የመተላለፊያ ኮሪደሮችን ልትደራደር ትችላለች፤ ነገር ግን አሰብ የኤርትራ ግዛት የማይነካና የተሟላ አካል በመሆኑ በላይዋ ላይ የባለቤትነት መብት መጠየቅ እንደማይችል አሳስበዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ ሀገራቸው ለኢኮኖሚያዊ ትብብር ሁልጊዜ ዝግጁ መሆኗን፣ ነገር ግን በማንኛውም ዓይነት የግዛት ጥያቄዎች፣ ጫናዎች እና ዛቻዎች ላይ ጥብቅ ተቃውሞ እንዳላት አስታውቀዋል።


ይህ
አቋም የአልጀርሱን ስምምነት፣ በዓለም አቀፍ ኮሚሽን የተደነገጉትን ድንበሮች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ግዛታዊ አንድነት የሚያከብር ሲሆን፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ ጭምር የሚደገፍ መርህ መሆኑን አንስተዋል።

በሌላ በኩል ጽሑፉ አሜሪካ በቀይ ባህር ያለውን የኢራን ማስፋፋት ፖሊሲ ለመግታት ሲባል ኢትዮጵያ የኤርትራ ወደብ እንዲኖራት ትደግፋለች የሚለውን የተሳሳተ ትንታኔ አጥብቆ አርሟል።


አምባሳደሩ ኤርትራ የኢራንም ሆነ የሌላው ኃይል መሣሪያ ወይም መጠቀሚያ እንዳልሆነች ገልጸው፤ ሀገራቸው ከኢራን ጋር ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላት ነገር ግን የራሷን ነፃ የውጭ ፖሊሲ እንደምትከተል እና ግዛቷን ለውጭ ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶች እንደማታስገዛ አስረድተዋል።

በቀይ
ባህር ላይ ሰላም እና ጸጥታ ሊሰፍን የሚችለው የባህር ዳርቻ ሀገራትን ሉዓላዊነት በማክበር እና ከውጭ ሀገራት ጣልቃገብነት በመጽዳት እንጂ ቀጠናውን ወደ ጦር አውድማ በመቀየር እንዳልሆነ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎረቤት ሀገር ጋር ወደ አዲስ ግጭት እና ውዝግብ ውስጥ ሳይገባ ሰላም፣ ዕርቅ እና ልማት እንደሚያስፈልገው ገልጸው፤ አሰብ የወል ልማት መሣሪያ ሊሆን የሚችለው በግልጽነት እና በሁለቱም አገራት ፍላጎት ላይ ብቻ በተመሠረተ ንግድ እንጂ በግፊት ሊሆን እንደማይችል በመግለጽ መልእክታቸውን ደምደዋል።

በቀይ ባህር እና በባህር በር ባለቤትነት ዙሪያ በቀጣናው ዲፕሎማሲያዊ ውዝግቦች እየተባባሱ ባለበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ብሔራዊ ጥቅም ከማንኛውም ድርድር በላይ የሚቆም «ቀይ መስመር» መሆኑን አበክሮ መግለጹ ይታወሳል።

 

በተጨማሪም ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የጊዜያዊ ፖለቲካ ወይም የፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን የሕዝቦችን ህልውና እና የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን የጋራ አጀንዳ መሆኑን ጠቁሞ ነበር።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።